Wednesday, March 25, 2015

በ12ኛ ክፈለ ጦር ለሚገኙ ወታደሮች ደመወዝ ለመክፈል ሲሄዱ የነበሩ አራት መኮነኖች። ከመተማ ወደ ኮር-ሁመር በሚወስደው መንገድ ላይ ተገድለው እንደተገኙ ከአካባቢው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣



እነዚህ በወታራዊ መኪና እየተጓዙ የነበሩ የ12ኛ ክፍለ ጦር የፋይናንስ ሰራተኛ የሆኑ አራት መኮነኖች መጋቢት 2/2007 ዓ.ም ከመተማ ወደ ኮር ሁመር በሚወስደው መስመር ላይ ሲደርሱ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች እንደተገደሉ የገለፀው ይህ መረጃ። ይዘውት የነበረው የክፍለ ጦሩ ጠቅላላ ደመወዝ። 4 ሽጉጥ፤ 4 ክላሽና ሌላም ንብረታቸውን ባልታወቁ ገዳዮች እንደተወሰደ ሊታወቅ ተችሏል፣
እነዚህ ለጊዜው ስማቸው ያልተገለፀው ሟቾች የስርዓቱ የወታደር አባላት ሁለት የፋይናንስ አባላት የሺህ አለቃ ማዕረግ ያላቸው። አንድ ሻንበልና አንድ ደግሞ የመቶ አለቃ ማዕረግ ያላቸው አራት መኮነኖች እንደሆኑ የደረሰን መረጃ አክሎ አስታውቋል፣