Wednesday, April 1, 2015

የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች። ችግራቸውን በትግራይ ክልል አስተዳዳሪዎች መፈታት ስላልቻለ። ከፌደራል በመጡ የበላይ ባለስልጣኖች። መጋቢት 7/2007 ዓ/ም ስብሰባ እንደተካሄደላቸው ተገለጸ፣



በትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ የአክሱም ከተማ ነዋሪዎች በመልካም አስተዳደር እጦት እየተሰቃየን ነን በማለት። በስርዓቱ ላይ ተቃውሞ ባስነሱበት ሰዓትና። የክልሉ ባለስልጣኖች ሁኔታውን ለማረጋጋት በመኮሩበት ግዜ። ህዝቡ በበኩሉ ችግሩ እያባባሳችሁት ነው በማለቱ ምክንያት። ከፌደራል ተልከው የመጡትን ፀጋይ በርሄና ሮማን ገብረስላሴ። መጋቢት 7/2007 ዓ/ም ህዝቡን እንደሰበሰቡትና። ለመንግስት ሰራተኞችም ደመቀ መኮነንና አርከበ እቁባይ እንደሰበሰቧቸው ለማወቅ ተችሏል፣
    የፌደራል ባለስልጣናት ባካሄዱት ስብሰባ ላይ በህዝቡ ከቀረቡት ጥያቄዎች መካከል። ለመሰረተ ልማት ተብሎ ከህዝቡ የተዋጣውን ገንዘብ በከተማዋ አስተዳዳሪዎች እንደተጠፋፋ በማስረጃ አስደግፈን ያቀረብነውን ክስ። የክልሉ ባለስልጣናት በማጠፋፋቱ ላይ እጅ ስለነበራቸው ፍርድ ቤት በነፃ ለቋቿል፤ መልካም አስተዳደርና ፍትህ ጠቅልሎ ጠፍቷል፤ በመንግስት ጽሕፈት ቤቶች ውስጥ አድልዎ ስለሚፈፀም በችግር ላይ ችግር ተደራርቦናል፤ በአባይ ወልዱ አንመራም የሚሉ እንደነበሩ። የተገኘው መረጃ አክሎ አስታውቋል፣
    የህዝቡን ገንዘብ ለግል ጥቅማቸው እውለውታል ከተባሉት ባለስልጣኖች መካከል። አበራ ሃይለማርያም፤ መጎስ ካሲል፤ ወ/ሮ ርግበ ሃይለ፤ ዳንኤል መንግስቱና ሌሎችም መሆናቸውን የገለፀው መረጃው። ከማዘጋጃቤት የተጠፋፉው ገንዘብም። አንዳንዶቹ 7 ሚሊዮን ሲያጠፋፉ ሌሎችም እስከ 10 ሚሊዮን ብር የሚደርስ አጠፋፍቷል በሚል ምክንያት ክስ ቢቀርብባቸውም። በአባይ ወልዱ አጋዥነት ያለምንም ማጣራት እንዲለቀቁ እንደተደረገና። በስብሰባው ላይ እንደተገለፀ። መረጃው አክሎ አስረድቷል፣