Wednesday, April 1, 2015

ገዥው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ስርዓት ወጣት ተማሪዎችን ወደ ውትድርና እንዲገቡ በሁሉም ክልሎች ትዕዛዝ እንዳወረደ ለማወቅ ተችሏል፣



   ምንጮቻችን እንደገለፁት ገዥው ስርዓት ነባር ወታደሮች ወደ ስደትና ወደ ተቃዋሚ ድርጅቶች እየጠፉ በመሆናቸው ከመጋቢት 1/ 2007 ዓ.ም ጀምሮ ሁሉም ክልሎች እያንዳንዱ ወረዳዎች ከ30 እስከ 40 የሚሆኑ ከ25 ዕድሜ በታች የሆኑ ወጣቶችን ከ6ኛ እስከ 8ኛ ክፍል የትምህርት ደረጃ የሚገኙ ተማሪዎችን መልምለው ወደ ወታደራዊ ማሰልጠኛ እንዲያስገቡ ትዕዛዝ እንደወረደ ለማወቅ ተችሏል፣
   ይህ ወደ ወትድርና የሚደረገው የተማሪዎች ምልመላ ከተቻለ በፍላጎት እንዲገቡ ካልተቻለ ደግሞ ከአስተዳዳሪዎች ጋር በመመሳጠር በሃይል አስገድደው እንዲያስታጥቋቸው መምሪያ ተሰጥቷቸው የተላኩ መኮነኖች በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ቅስቀሳ እያደረጉ  ትምህርታቸውን እያደናቀፉ እንደሚገኙ  የደረሰን መረጃ አመለከተ፣