Wednesday, April 1, 2015

በኦሮሚያ ክልል ቢሾፍቱ ከተማ በደብረዘይት ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ይማሩ የነበሩ በርካታ ተማሪዎች ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ ሰንካላ ምክንያት እየተፈጠረ ከትምህርት ገበታቸው መባረራቸውን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን ገለፁ፣



እንደምንጮቻችን ዘገባ በኮሎኔል ሃጎስ ዲንነት የሚመራው  የደብረዘይት  ኢንጂነሪንግ ኮሌጅ ውስጥ ከሚገኙት ከ10 በላይ ክፍሎች መካከል የፕሮዳክሽና የኬሚካል ኢንጂነሪንግ ክፍል በብቃት ይከታተሉ የነበሩ  ተማሪዎችን ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ ምክንያት እየተፈጠረ ከትምህርት ገበታቸው መባረራቸውን  አስረድተዋል፣
በኬሚካል ኢንጂነሪንግ ክፍል ዲን መቶ አለቃ አማኑኤል የተባለ         ሰንካላ ምክንያት ተፈጥሮ ከትምህርት ገበታቸው ከተባረሩት   በርካታ ተማሪዎች መካከል ወጣት እንዳልክና ሳሙኤል የተባሉ የ3ኛ ዓመት ተማሪዎች እንደሚገኙበት ለማወቅ ተችሏል፣