Wednesday, April 8, 2015

በማዕከላዊ እዝ በ8ኛ መካናይዝድ ውስጥ። በወታደራዊ ሞያ ሲያገለግሉ የቆዩትን ወታደሮች። የነበሩበትን ቦታ እየለቀቁ በመጥፋት ላይ በመሆናቸው ምክንያት። በውስጣቸው ከፍተኛ ክፍተት ተፈጥሮ እንደሚገኝ ምንጮቻችን አስታወቁ፣



   በደረሰን መረጃ መሰረት።- በማዕከላዊ እዝ በ8ኛ መካናይዝድ የቅድመ ግንባር ሰራተኛ /ኦፒ/ ሆነው ሲሰሩ የነበሩ የስርዓቱ ወታደሮች።-በስርዓቱ ላይ ያላቸው እምነት እጅግ የወረደ በመሆኑ። ቦታቸውን እየለቀቁ ወደ ትውልድ ቦታቸውና ወደ ተለያዩ የተቃዋሚ ድርጅቶችና ጎረቤት ሃገሮች በመሰደድ ላይ እንደሚገኙ ሊታወቅ ተችሏል፣
በኦፒ ስራ ላይ ተመድበው ሲሰሩ ከቆዩትና ነገር ግን በአሁኑ ሰዓት በሃላፊዎቻቸው ግፍ ከተፈፀመባቸውና ከጠፉት የሰራዊት አባላት ውስጥ ምክትል መቶ አለቃ ወንድ ወሰን፤ አስር አለቃ ጴጥሮስ ተካና ሌሎችም ሲሆኑ። እነዚህ ወታደሮች በመጥፋታቸው ምክንያትም የመካናይዝድ አዛዦቹ የተፈጠረውን ክፍተት ስላስጨነቃቸው። ከነሱ ጋር ለነበሩ ሰዎች እያስፈራሯቸው እንደሚገኙ ምንጮቻችን አክለው አስታውቀዋል፣