Wednesday, April 8, 2015

በሰሜን ጎንደር ዞን አብርሃ ጅራ በተባለው ቦታ የሚኖሩ ወገኖች። የትጥቅ ትግል ከሚያካሂዱ ድርጅቶች ጋር ትተባበራላችሁ በሚል ምክንያት። መኖርያ ቤታቸው በስርዓቱ ታጣቂዎች እየተፈተሸ መሆኑን ተገለጸ፣



በአማራ ክልል ሰሜን ጎንደር ዞን፤ ዳንሻ አካባቢ አብርሃ ጅራ በተባለው ቦታ ውስጥ የሚገኙትን ባለ ሃብቶች። የትጥቅ ትግል ከሚያካሂዱ ድርጅቶች ጋር እየተባበሩና እየተቀላቀሉ ናቸው በሚል ምክንያት። በስርዓቱ ታጣቂዎች በሌሊት መኖርያ ቤታቸው እየተፈተሸ መሆኑን ምንጮቻችን ከቦታው አስታወቁ፣
   መረጃው በመጨረሻ። የኢህአዴግ ባለስልጣኖች በላያቸው ላይ የሚካሄደው ህዝባዊ ትግል ከግዜ ወደ ግዜ እየተጠናከረ መሄዱን ስለተገነዘቡ። ሰላማዊ ህዝቡን ልጆቻችሁ የትጥቅ ትግል ወደሚያካሂዱ ድርጅቶች እየተቀላቀሉ ሲሆኑ። እናንተም ለትግሉ እየተባበራችሁ ናቸሁ በማለት። እያጋላትዋቸው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፣