Saturday, April 18, 2015

በአማራ ክልል የሚገኘውን ህዝብ። የአምባገነኑ ስርአት ካድሬዎች በምርጫው ላይ ድጋፍ እንዲያገኙ በማለት። ተግባር ላይ የማይውል ቃል እየገቡለት መሆናቸው ተገለጸ፣



ስርዓቱ በምርጫው ዋዜማ ህዝብን በማደናገር ስራ ላይ መሰማራት ዋና መለያው መሆኑን የገለጸው መረጃው። በአማራ ክልል ለሚገኘው ህዝባቸን። መሬት የሌለውን ሰው የመሬት ባለቤት አናደርገዋለን፤ የመሬት ግብር እንቀንሳለን፤ ማዳበርያ በርካሽ ዋጋ ወደ ህዝቡ እናቀርባለን፤ ያለውን የመልካም አስተዳደር ችግር እንፈታዋለን በማለት የስርአቱ ካድሬዎች ተግባር ላይ የማያውሉ ቃሎችን እየገቡለት ቢሆንም። ህዝቡ ግን እንዳልተቀበላቸው ለማወቅ ተችሏል፣
   የኢህአዴግ ቡድን በምርጫ ላይ የህዝብ ድጋፍ ለማግኘትና ለማሸነፍ በማሰብ። ተቃዋሚዎች እንዳይንቀሳቅሱ እድል አሳጥቶ። በየደረጃው የሚገኙትን ማለት የመንግስት ሰራተኛ፤ ተማሪዎች፤ አርሶ አደሮችና ሌሎችንም የህብረተሰብ አካላት በመሰብሰብና በመቀስቀስ ስራ ላይ ቢጠመድም። እስካሁን ግን በአብዛኛው አካባቢዎች ከባድ ተቃውሞ እያጋጠመው መሆኑን የተገኘው መረጃ አክሎ አስርድቷል፣