Saturday, April 18, 2015

በባድመ አካባቢ የሚገኘው ህዝባችን አንድ ለአምስት በሚል የስርአቱ አደረጃጀት ተሰባስቦ። ከወታደሮች ጋር በመሆን ምሽግ እንደሚቆፍርና ንብረቱን ወደ ኋላ እንዲያጓጉዝ እየተደረገ መሆኑን ተገለፀ፣



በመረጃው መሰረት። በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን። ባድመ አካባቢ የሚገኘውን ህዝብ። ጠላት ምርጫችንን ለማሰናከልና ለማጥቃት እየተዘጋጀ ስለሆነ የአካባቢው ህዝብ ከ 22ክፍለጦር ጋር ሆኖ ምሽግ እንዲቆፍር በማለት በኢህአዴግ ባለስልጣኖች እየተገደደ መሆኑን የገለፀው መረጃው። በተጨማሪም ከፍተኛ ንብረት ያለው ሰው ጥቃት ከመድረሱ በፊት ንብረቱን ወደ ኋላ እንዲያጓጉዘው እያስፈራሩት መሆናቸውን የተገኘው መረጃ አስታውቋል፣
    መረጃው አክሎም። የባድመ ነዋሪ የሆነው ህዝብ። የግል ኑሮውን በመተው ከወታደሮቹ ጋር ሆኖ ምሽግ እንዲቆፍር እየተገደደ መሆኑንና። ነዋሪው በበኩሉም ጉልበታችን በነፃ እየባከነ ኑሮአችንን መምራት አልቻልንም በማለት ብሶቱን እየገለጸ መሆኑን መረጃው አክሎ አስርድቷል፣