በምንጮቻችን መረጃ መሰረት። በትግራይ ምእራባዊ
ዞን ሁመራ ከተማ የሚኖር ህዝብ። ከመቐለ በመጡት የህወሃት/ኢህአዴግ ከፍተኛ ባለስልጣናት። ሚያዚያ 9/ ቀን/ 2007ዓ/ም ስብሰባ ማካሄዳቸውን የገለጸው መረጃው። የስብሰባው አጀንዳም የመልካም አስተዳደርና
የህግ የበላይነት እንዴት እየተሰራበት ነው በሚል እንደሆነና። ተሰብሳቢዎች በፊናቸው በከተማችን የመልካም አስተዳደርና የህግ የበላይነት
ከስር መሰረቱ ከጠፋ አመታትን አስቆጥረዋል በዚህም ምክንያት ተገልጋይ ህብረተሰብ ሰሚ አጥቶ ተቸግሮ መኖር አማራጭ አድርጎት ይገኛል
የሚል መልስ እንደመለሱሏቸው ታወቋል፣
ተሰብሳቢዎቹ በመቀጠል። የሁመራ ከተማ ህዝብ ሃብታም እያለ የደሀየ ህዝብ
ሆነ፤ የመሰረተ ልማት ተጠቃሚ መሆን አልቻለም፤ ራሱ ሰርቶ ኑሮውን እንዳያሻሽል። አስተዳዳሪዎቹ የህዝቡን አጋዦች ከመሆን ይልቅ ራሳቸው ችግር ፈጣሪዎች እየሆኑ ናቸው ይህ ተግባርም
የአተዳዳሪዎቹ ብልሹ አካሄድ የወለደው ነው በማለት ምሬታቸውን እንደገለፁ ለማወቅ ተችሏል፣
በተፈጠረ ችግር ዋነኛ ተጠያቂዎች የሆኑ አስተዳዳሪዎችና የፍትህ አካላት
እየተነሳ ያለውን የህዝቡ ችግር ሰምተው ማሻሻል ሲገባቸው። ሃሳባችን በማቅረባችን ብቻ። በቀጥታና በተዘዋዋሪ ስልጣናቸው ተጠቅመው
እየረገጡንና እያገለሉን ናቸው በማለት ያላቸው ስጋት መናገራቸውን መረጃው አክሎ አብራርቷል፣