በትግራይ ምስራቃዊ ዞን አዲግራት ከተማ ከጊዜ
ወደ ጊዜ እየከፋ እየሄደ ያለው የመጠጥ ውሃ እጥረትና የመሰረታዊ አላቂ ነገሮች በስልጣን ላይ የሚገኘው ገዢው ስርዓት መፍትሄ ሊያደርግበት
አለመቻሉን የገለፀው መረጃው። በዚህ ምክንያትም በከተማው የሚኖረው ማህበረሰብ እለታዊ ኑሮውን ለመምራት ተቸግሮ እንደሚገኝ ለማወቅ
ተችሏል፣
በመረጃው መሰረት ነዋሪው ህዝብ ንፁህ የሚጠጣ ውሃ ካጣ አመታትን ያስቆጠረ
ችግር ሲሆን ከላይ እስከ ታች የሚመለከታቸው የስርዓቱ ባለስልጣናት ችግሩን እያወቁ መፍትሄ ከማስቀመጥ ይልቅ የማይተገበሩ ቃል እየገቡ
መሆናቸው ታውቋል፣
ይህ የመሰረታዊ ነገሮችን እጥረቱ ለመፍታት በሚል ለነዋሪው ህዝብ በተሻለ
ዋጋ እንዲከፋፈል ተገዝቶ ወደ ከተማዋ የገባውን ከተጠቃሚዎች ዘንድ ሳይደርስ አስተዳዳሪዎች ከሸሪኮቻችው ጋር በመሆን ለግል ጥቅማቸው
እያዋሉት ነው ተብሎ በተደጋጋሚ አቤቱታ ቢቀርብም። እስካሁን ምንም ዓይነት እርምጃ እንዳልተወሰደና ችግሩ እየከፋ መሄዱ መረጃው
አክሎ አስረድቷል፣