Thursday, April 23, 2015

በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን በርካታ ንፁሃን ዜጎችን እየወነጀለ የሃሰት ምስክርነት እንዲያቀርብ እየተገደደ መሆኑ ተገለፀ፣



በስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን እንደገለፁት በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቴሌኮሚዩኒኬሽን ኮርፖሬሽን በርካታ ንፁሃን ዜጎችን እየወነጀለ  በሃሰት የተቀናበረ የድምፅ ሙሌት ለፍርድ ቤቶች የምስክርነት ቃል እንዲያቀርብ በድርጅቱ ሃላፊ      በአንዷለም አድማሴና በተዛማጅ አመራሮች እየተገደደ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣
ይህ በእንዲህ እያለ የኢትዮጵያ ቴሌኮምኒኬሽን ኮርፖሬሽን ሰራተኞች የሚተላለፉ መልዕክቶችን መቅረፅ ከሚችለው ዘመናዊ መሳሪያ ውጭ በዜጎቻችን ላይ ተጨማሪ የምናደርገው የሃሰት ሙሌት ተቀባይነት የለውም ከድስፒሊን ውጭና የሰውችን ሰብአዊ መብትን የሚጥስ ነው በማለት መቃወማቸውን ታውቋል፣
 የደረሰን መረጃ ጨምሮም ከአመታት በፊት ቅነሳ በሚል በርካታ የተባረሩ የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች ምክንያቱ ቅነሳ ሳይሆን ዜጎችን በሃሰተኛ የድምፅ ሙሌት ለፍርድ ቤት የምስክርነት ቃል እንዲያቀርቡ ታዝዘው ባለመተግበራቸው ሲሆን ዛሬም ይህ እድል እንዳይገጥማቸው በቦታው የተመደቡ ሰራተኞች ሳይወዱ በግድ ከስራ ላለመባረር እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፣