Wednesday, April 8, 2015

በመቐለ ከተማ የሚኖር ህዝባችን በመሰረታዊ አላቂ ነገሮች ተቸግሮ ባለበት በአሁኑ ሰዓት የስርዓቱ ካድሬዎች በህብረተሰቡ ስም የሚመጣውን መሰረታዊ አቅርቦት ለግል ጥቅማቸው እያዋሉት በመሆናቸው ህዝቡ ምሬቱን እየገለፀ እንደሆነ ታወቀ፣



   በመቐለ ከተማ የሚኖር ህዝባችን በማህበራዊ ጉዳዮች ተቸግሮ ብሶቱን እየገለፀ ባለበት በዚህ ሰዓት። ነዋሪው ህዝብ ከሚያገኛቸው ሱቆች በተሻለ ዋጋ እንዲገዛ ተብለው የመጡትን እንደ ዘይት፤ ስኳር፤ የፊርኖ ዱቄት፤ ወዘተ የመሳሰሉ መሰረታዊ አላቂ ነገሮች የከተማዋ ካድሬዎች ለማታለያ የተወሰነ ወደ ቀበሌዎች በማከፋፈል አብዛኛውን ለግል ጥቅማቸው ስለሚያውሉት። በከተማዋ ለ3 ሊትር ዘይት ከ260 እስከ 300 ብር እየተሸጠ እንደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል፣
   በስርዓቱ ካድሬዎች እየተካሄደ ያለውን ብዝበዛ የከተማው መላው ህብረተሰብ ስላወቀው። መጋቢት19/2007 ዓ.ም የተቃውሞ ሰላምዊ ሰልፍ ለማካሄድ ጥያቄ እንዳቀረበ የገለፀው ይህ መረጃ። ካድሬዎችና አስተዳዳሪዎችም በነዋሪው ህብረተሰብ የተነሳውን ህዝባዊ ተቃውሞ ለማሰናከል በስብሰባ ላይ ተጠምደው የሚገኙ ሲሆን። ነዋሪው ህዝብ  በፊናው። ለምንድንነው በዜጎች ህይወት ላይ የምትቀልዱት? ሰላማዊ ሰልፍ እንዳናካሄድ የተከተላችሁት መንገድ፣ የህዝቡን ልሳን የሚያፍን ነው በማለት የከተማዋ ነዋሪ ህዝብ ምሬቱን በተቃውሞ መልክ እያሰማ እንደሚገኝ ከከተማዋ የሚገኙ ምንጮቻችን አስረድተዋል፣