Wednesday, April 8, 2015

በሁመራ ከተማ የሚገኙ መምህራን ከምርጫ ጋር በተየያዘ ምክንያት የከተማዋ አስተዳዳሪዎች በስብሰባ ላይ ጠምደዋቸው እንደሰነብቱ የደረሰን መረጃ አመለከተ፣



   በከተማዋ የሚገኙ ምንጮቻችን እንደገለፁት።- በሁመራ ከተማ የሚገኙ የአንደኛና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት መምህራን ሁሉንም በጅምላ አለሙ አየነው የተባለ የከተማዋ አስተዳዳሪ እንደሰበሰባቸው የገለጸው መረጃው። የስብሰባው አላማም በመጭው ግንቦት ወር ላይ ለሚካሄደው አስመሳይ ሃገራዊና ክልላዊ ምርጫ በትምህርት ቤቱ ውስጥ የሚማሩ ተማሪዎችና መምህራን በህወሃት ኢህአዴግ ላይ ያላቸው እምነት ምን ይመስላል? ሊመርጡን ይችላሉ ወይ? የሚሉና ሌሎችንም ሃሳቦች ለመገምገም የታቀደ እንደነበር ምንጮቻችን አክለው ገልፀዋል፣