እንደመረጃው ዘገባ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የትግራይ፤ የአማራና የኦሮሚያ
ክልል ተወላጅ የሆኑ ኢንቨስተሮችና ባለሃብቶች ለበርካታ አመታት ሲያለሙበት
የቆዩትን መሬታቸውን እየለቀቁ ወደ የክልላቸው እንዲወጡ እየተደረገ መሆኑን የገለፀው መረጃው። እንዲለቁ በአስገዳጅነት ከቀረቡ ምክንያቶች
መካከልም መጪውን ምርጫ በክልላቸው ሂደው እንዲመርጡ የሚል ትዕዛዝ በመተላለፉና በክልሉ የሚገኘው ሰፊ የእርሻ መሬት በአንድ ባለሃብት
ስር መያዝ አለበት የሚሉና የሌላ ክልል ተወላጅ የሆኑት ባለሃብቶች የክልሉ መንግስት ጫና ፈጠረብን የሚል አቤቱታ ማቅረባቸውን ተከትሎ
የቀረበ ማስመሰያ መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣
መረጃው ጨምሮም ማስጠንቀቂያ ከተሰጣቸው በርካታ ወገኖች መካከልም አቶ በሪሁን አብዩ የተባለው
የአማራ ክልል ተወላጅ የአዊ ዞን ባለሃብት እንደሚገኝበት አስረድተዋል፣