Wednesday, April 1, 2015

ደቡብ ክልል ወልቂጤ አካባቢ በሚገኙ ወረዳዎች የሚሰሩ የሌላ ክልል ተወላጅ የመንግስት ሰራተኞች ከመጪው ምርጫ ጋር በተያያዘ ማስፈራሪያ እየደረሳቸው መሆኑን ምንጮቻችን አስረዱ፣



 በወልቂጤ አካባቢ ሁራአክሊል ሃዋሪያ በተባለው ወረዳ በሚገኙ የመንግስት ሰራተኞች ላይ ከፍተኛ ማስፈራራት እየደረሰባቸው መሆኑን የገለፀው መረጃው የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አለም ይርጋና የወረዳው የድርጅት ጉዳይ ሃላፊ አንድ ላይ በመሆን በማስፈራራት ተግባር ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፣
 ማስፈራራት እየደረሰባቸው ከሚገኙ የሌላ ክልል ተወላጆች የወረዳው ሰራተኞች መካከል ይሁን የተባለው የወረዳው የግብርና ጽሕፈት ቤት የግብዓት የስራ ሂደት  ባለሙያና ለጊዜው ስማቸው እንዲጠቅስ ያልፈለጉ የትምህርት ጽሕፈት ቤት ሰራተኞች ከመጋቢት 11 /2007 ጀምሮ የምርጫ ካርድ ካለማውጣታቸው ጋር ተያይዞ እንደሚባረሩ በክልሉ መስራት እንደማይችሉ አለምሰገድ በተባለ የስርዓቱ ተላላኪ የተነገራቸው መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፣