Friday, April 17, 2015

በኦሮሚያ ክልል የሻንቡ ከተማ ነዋሪዎች በኦህዴድ/ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ካድሬዎች የተደረገላቸውን የስብሰባ ጥሪ እንዳልተቀበሉት ተገለጸ፣



    ምንጮቻችን ከስፍራው እንደገለፁት። መጋቢት 26 ቀን 2007 ዓ/ም ለሻንቡ ከተማ ነዋሪዎች በስርዓቱ ካድሬዎች የተደረገ የስብሰባ ጥሪ። እንዳልተቀበሉት ከገለፀ በኋላ። በህዝቡ እምቢታ የተቆጡት የከተማው አስተዳዳሪዎች። ስግብግብ ፖሊሶችን በማሰማራት በግፍ እየቀጠቀጡ ወደ ስብሰባው እንዲወጣ ያደረጉት ሲሆን በአንፃሩ ተቃዋሚ ድርድቶች መጋቢት 27 /2007 ዓ/ም የምረጡኝ ቅስቀሳ ለማካሄድ በወጡበት ሰዓት። ነዋሪው ህዝብ አበባና ወተት በመያዝ በድምቀት እንደደገፋቸው  ለማወቅ ተችሏል፣
   ህዝቡ በተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ ያለው አመለካከት። ያሰጋቸው  የስርዓቱ ካድሬዎችም ለልማት ለወጣው መንግስታችን ተቃውማችሁ ለምን በተግባር ላልተፈተኑ ተቃዋሚዎች ትደግፋላችሁ ሲሉ ያቀረቡትን ሃሳብ። ህዝቡ በበኩሉ ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ያለማው የለም ለምቷል የምትሉትም ለግል ጥቅማችሁ ያዋላችሁትን የህዝብንና የሃገርን ንብረት እንጂ በእናንተ የመጣ ለውጥ የለም ሲሉ ጥላቻቸውን መግለፃቸውን ለማወቅ ተችሏል፣