Friday, April 17, 2015

የላዕላይ አድያቦ ወረዳ፤ ምድረ ፈላሲ ቀበሌ ነዋሪ የሆኑ ወገኖቻችን። የትህዴን ተባባሪዎች ናችሁ እየተባሉ። በስርአቱ እየታሰሩና ግፍ እየደረሰባቸው መሆኑን ተገለፀ፣



    በትግራይ ሰሜናዊ ምእራብ ዞን፤ ላዕላይ አድያቦ ወረዳ፤ የምድረ ፈላሲ ቀበሌ ነዋሪዎች የሆኑ ንፁሃን ዜጎቻችን። ለትግራይ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ ተባባሪዎች ናችሁ ተብለው እየታሰሩና ግፍ እየደረሰባቸው መሆኑን የገለፀው መረጃው። ከታሰሩት ወጎኖቻችን ውስጥም።- የምድረ ፈላሲ ቀበሌ አስተዳዳሪ የነበረው አርአያ ይግዛው፤ ገብረአምላኽ ካሕሳይ፤ ሕመድ አሕመድ፤ ስራጅ መሓመድ፤ ሓጎስ ለገሰ፤ አስግዶም ከሰተ፤ ሃደራ ብርሃነ፤ ግደይ ሃደራ፤ ክብሮም ኪሮስ፤ ተስፋሁነይ ሃይለ፤ ፍስሃየ ስብሃቱና ሌሎችም እንደሚገኙባቸው የደረሰን መረጃ አስታወቀ፣
   ይህ በአምባገነኑ የህወሃት/ኢህአዴግ ስርአት። ንፁሃን ዜጎቻችንን የማሰርና በላያቸው ላይ ግፍ የመፈፀም ተግባር። በላዕላይ አድያቦ ወረዳ  ብቻ ሳይሆን። በመላው የአገራችን አካባቢዎች እየተፈፀመ ያለ የመብት ጥሰት መሆኑ ይታወቃል፣