Monday, April 6, 2015

ገዥው የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት በቅርቡ ለሃገሪቱ ዜጎች ይፋ ያደረገውን የጦር መሳሪያ ምዝገባ ተከትሎ በተላላኪ ፖሊሶቹ አማካኝነት የንፁሃን ዜጎችን ህይወት ማጥፋት መጀመሩን ምንጮቻችን ከተለያዩ የአገራችን አከባቢዎች ገለፁ፣



   አምባገነኑ የኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት በቅርቡ በአማራ ክልል በተለያዩ ዞኖች ከመጋቢት 18 እስከ ሚያዝያ 14/ 2007 ዓ/ም ባለው ጊዜ ውስጥ ማንኛውም የግልና የመንግስት የጦር  መሳሪያ የታጠቀ ሁሉ በአቅራቢያው በሚገኝ የአስተዳደርና ፀጥታ ዘርፍ ጽሕፈት ቤት ማስመዝገብ እንዳለበት የተገለፀ ሲሆን ለምዝገባ የሚከፈለው ገንዘብም ለክላሽን ኮፍ መሳሪያ 35 ብር እንዲሁም ለሽጉጥ እንደየአይነቱ  ከ300 ብር ጀምሮ እንደሚከፈል መገለፁን ተከትሎ አንዳንድ የገዥውን መንግስት ደካማ ጎን በግልፅ የሚናገሩ ታጣቂዎች ለማስመዝገብ በሄዱበት እየታሰሩና እየተገደሉ  መሆናቸውን ለማወቅ ተችሏል፣
     የገዥውን መንግስት የጦር መሳሪያ የምዝገባ ትዕዛዝ በማክበር ለማስመዝገብ ከሄዱትና ታስረው ከተገደሉት ንፁሃን ዜጎች መካከል በአዊ ዞን፤ አንከሻ ወረዳ፤ አዘና ቀበሌ ውስጥ። ተመስገን የኔው የተባለው አባወራ ለበርካታ አመታት ሲጠቀምባት የቆየውን ማካሮቭ ሽጉጥ መሳሪያውን ለማስመዝገብ በሄደበት ግዜ አሸባሪ ነህ  ወጣቶችንም ታደራጃለህ በሚል። ኢንስፔክተር አዳነና ኢንስፔክተር አየነው ሞነን እንዲሁም ከሶስቱ ሹማታ ቀበሌ ሊቀመንበር ጋር በመሆን በሌሊት የገደሉት ሲሆን። ተከታዩ ናቸው በሚል እንጂባራ ከተማ ውስጥ የሚገኙት አቶ አለህኝ የኔውና አቶ ትዕዛዙ አለሙ የተባሉትን ራሳቸው ፖሊሶቹ በሃሰት መስክረው ለ18 ዓመት እንዲፈረድባቸው ማድረጋቸውን መረጃው አክሎ አስረድቷል፣