Monday, April 6, 2015

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ጉባ ወረዳ ወደ ህዳሴ ግድብ በሚወስደው መንገድ ዳር ላይ ሰፍረው የሚገኙ ንፁሃን ዜጎች በአሸባሪነት ስም መታሰራቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣




  መረጃው እንዳመለከተው በክልሉ መተከል ዞን ጉባ ወረዳ ማንኩሽ በተባለው አካባቢ  ይኖሩ የነበሩ ሁለት ለጊዜው ስማቸው በወል ያልታወቁ የአማራ ክልል ተወላጅ የሆኑ አርሶ አደር ወጣቶችን ከ6 ዓመታት በላይ ሲኖሩበት የቆዩትን ቤት ለምን መንገድ ዳር ሰራችሁት በትጥቅ ትግል ለሚንቀሳቀሰው የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ህዝቦች ነፃ አውጭ ንቅናቄ  (ቤ.ህ.ኒ.ን) የተባለው ድርጅት  ተላላኪ አሸባሪ ናችሁ በማለት ቤታቸው እንዲፈርስ ከተደረገ በኋላ በቅርቡ 4ኛ አመት  የህዳሴ ግድብን በዓል ለማክበር የተንቀሳቀሰውን ህዝብ ለማሸበር አሲራችኋል ተብለው መጋቢት 23 ቀን 2007 ዓ/ም  ባልታወቁ ተላላኪ  የፌድራል ፖሊሶች ተይዘው መወሰዳቸውን ከስፍራው የደረሰን መረጃ አመለከተ፣
   ከክልሉ ሳንወጣ ገዥው መንግስት በአሶሳ ከተማ የሚኖሩ ህዝቦችን ኢ.ህ..አ.ዴ.ግን ካልመረጣችሁ ከተሰማራችሁበት የኢንቨስትመንትና የግል እርሻ እናፈናቅላችኋለን በማለት እያስፈራራቸው ሲሆን ማህበረሰቡ ግን ምንም ዓይነት የዲሞክራሲ መረጋጋት በማይታይባት ቤንሻንጉል እንዴት ምርጫ ሊካሄድ ይችላል በማለት ምርጫውን እየተቃወመ መሆኑን ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን አስረድተዋል፣