Thursday, April 16, 2015

በደቡብ ብሄር ብሄረ ሰቦች ክልል ሸካ ዞን የኪ ወረዳ የሚገኙ የስርዓቱ ወሮ በላ ካድሬዎች ለተቃዋሚ ድርጅቶች ደጋፊና አባሎችን እያሰቃዩዋቸው እንደሚገኙ ታወቀ፣



እንደምንጮቻችን መረጃ መሰረት።- በየኪ ወረዳ የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅቶች ደጋፊ የሆኑ ባለሃብቶች  ፀረ ህዝብ በሆነው በደህዴን ኢህአዴግ ስርዓት በላያቸው ላይ ግፍ እየተፈፀመ እንዳለ ከገለፁ በኋላ። የትግስት ሆቴል ባለቤት የሆነውን አቶ ብዙአየሁ ተገኝ የተባለ ባለሃብት መጋቢት 18/2007 ዓ/ም ከምሽቱ 4።00 በቤቱ በራፍ ላይ ቁሞ እያለ የስርዓቱ ወሮ በላ ካድሬዎች በስለት ወግተውት እንዳመለጡ ሊታወቅ ተችሏል፣
   ይህ በእንዲህ እንዳለ ማሙሽ ቢያድግልኝ ለተባለው የመድረክ አባል የሆነውን ወገን በሚንቀሳቀስበትን ቦታ በማድባት የደበደቡት ሲሆን። መምህር ሉቋስ ወንድሙ የተባለውን ደግሞ “በጠበንጃ ያዥ” ትምህርት ቤት የሚያስተምረውና የቤንች ህዝቦች ንቅናቄ ድርጅት አባል የሆነውን ወገንም ስለ ድርጅቱ የሚመለከቱ አንዳንድ ቅስቀሳዎችን ለህዝቡ እያደረገ በነበረበት ሰዓት። በታጣቂዎች ተይዞ የታሰረ ሲሆን። በሌሎች ዜጎቻችን ላይ ደግሞ ሰፊ የማስፈራራት ዘመቻ እየተደረገ እንደሚገኝ ምንጮቻችን አስረድተዋል፣
   እንደዚህ አይነት አስነዋሪ ተግባር ከምርጫ ጋር በተያያዘ የስርዓቱ ካድሬዎች በተቃዋሚ ድርጅቶች አባላትና ደጋፊዎች ላይ የሚፈፅሙት ተግባር መሆኑ አዲስ እንዳልሆነ በመግለፅ። ይህ የማስፈራራትና የመግደል ድርጊትም በሃገር አቀፍ ደረጃ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ ያለና ተጠናክሮ በመቀጠል ላይ የሚገኝ ጉዳይ መሆኑን ምንጮቻችን አክለው ገልፀዋል፣