Thursday, April 16, 2015

በመረብ ለኸ ወረዳ ዓዲ ማሓይሽ የሚኖሩ የዓረና ተቃዋሚ ድርጅት አባላት የሆኑ ወገኖቻችን። ከትህዴን ጋር ግንኙነት አላችሁ ተብለው እንደታሰሩ ተገለፀ፣



   በትግራይ ማዕከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ ዓዲ ማሓይሽ የሚኖሩ የዓረና ድርጅት አባላት የሆኑ ወገኖቻችን የትህዴን ደጋፊዎችና ተባባሪዎች ናችሁ ተብለው የህወሃት ኢህአዴግ አስተዳዳሪዎች ፖሊሶችንና ወታደሮችን በመያዝ በሌሊት ወደ ቤታቸው በመግባት በመፈተሽና በማሰር ስራ ላይ ተጠምደው እንደሚገኙ ከአካባቢው የሚገኙ ምንጮቻችን አስታወቁ፣
   ከታሰሩት ወገኖቻችን የተወሰኑትን ለመጥቀስ።- ወጣት ዘሚካኤል ተስፋ ስላሴ፤ አስመላሽ ጉዑሽና ወልደገብርኤል ገብረፃዲቅ የተባሉ የሚገኙባቸው ሲሆኑ የስርዓቱ ካድሬዎች ከፀጥታ አካላትጋር በመተባበር ባለፈው መጋቢት ወር በሌሊት ከመኖሪያ ቤታቸው አፍነው የወሰዷቸው ሲሆን። ራማ ከተማ አንድ ሌሊት አሳድረው ወደ መቐለ ከተማ እንደወሰዷቸው ምንጮቻችን አክለው ገልፀዋል፣