Friday, June 19, 2015

የትግራይ ክልል ምእራባዊ ዞን ፍትህና አስተዳደራዊ አገልግሎት ለማግኘት ጉቦና ሌሎች ጥቅማጥቅም ለመስጠት እንደ ምትገደድ የዞኑ ነዋሪዎች ገለፁ።



      እንደ ምንጮቻችን መረጃ መሰረት።- ከክልል አስተዳደር የተላኩት በኪሮስ ቢተው የተመሩት የህወሓት/ኢህአዴግ ባለስልጣናት በትግራይ ምእራባዊ ዞን የሚኖር ህዝብ በመሰብሰብ የፍትህ አገልግሎቱ ምን ይመስላል? ብለው ባቀረቡት የመጀመሪያ የመወያያ አጀንዳ ላይ ተሰብሳቢዎች በበኩላቸው “ፖሊስ ህጋዊ መደበኛ ስራቸው በመተው በግቦ፤ ኮንትሮባድንና የተለያዩ ጥቅማጥቅም በመሰብሰብ በአጭር ጊዜ ኢንቨስተሮች ሁነው እንደሚገኙ ሰለዚህም ፍትህ ለማንገስ የሚሰራ አካል ስለሌለ ፍትህ በገንዘብ እየተሸጠ ነው።” ብለው እንደ ተናገሩ ታውቋል።
   መረጃው በማከል ከግንቦት 28/ 2007ዓ/ም ጀምረው የዞንና የወረዳ አስተዳዳሪዎች ምን ላይ ይገኛሉ? የሚልና  ሁለተኛ የመወያያ አርእስት ብለው ባቀረቡት ሃሳብም በአማራ ክልልና በትግራይ ክልል መካከል ተከስቶ ባለው መፍትሄ ያጣ ግጭት  የዞኑ ዋና አስተዳደር አቶ ፍስሃ በርሀ ከግጭቱ በፊትና ብኋላ ሃላፊነቱ ስላልተዋጣ ዋናው ቀስቃሽ እሱ እሱ ራሱ ነው ብለው በሃላፊው ፊት ሂስ እንዳቀረቡለት ለማወቅ ተችሏል።
  ከፍስሃ በርሀ ጋር በተሳሰረም ለጊዜው ስሙ ያልታወቀ የከተማ ልማት ሃላፊና የማሃንዲሶች አስተባባሪ የሆነው ግለሰብ ከ3 ሚልዮን ብር በላይ በልቶ በሁመራ ከተማ ታስሮ እንደሚገኝና ፍስሃ በርሀ በበኩሉም ከሃላፊነቱ ተወግዶ ስራውን በምክትሉ እያተሰራ እንደሚገኝ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።