Friday, June 19, 2015

በሑመራ ከተማ የሚገኙ ስርዓቱን ያሰማራቸው ታጣቂዎች አሸባሪ ገብቶውብናል በማለት ከባድ ፍተሻ ማካሄዳቸው ታወቀ።



   በምንጮቻችን መረጃ መሰረት የኢህአዴግ አፋኝ ቡዱን ወደ ሑመራ ከተማ አሸባሪዎች ገብቶዋል በሚል ሽፋን ሰኔ 1/2007 ዓ/ም ፌደራል ፖሊስ፤ ልዩ ሃይል፤ የመከላከያ ሰራዊትና ሌሎች የፀጥታ አካላት በማሰማራት በከተማው ውስጥ የሚገኙ የተለያዩ ተሽከርካሪዎች እንዳይንቀሳቀሱ መከልከላቸውንና አቁመው እንዲፈተሹ ማድረጋቸው የገለፀው መረጃው ህጋዊ ባልሆነ መንገድ በየመኖርያ ቤቱና የንግድ ድርጅቶችን እየፈተሹና ነዋሪውን ህዝብ እያስፈራሩ መዋላቸውን የተገኘው መረጃ አስታውቋል።
  ይህ በገዢው ስርዓት የተካሄደውን ፍተሻ በከተማው ውስጥ ምንም አይነት ችግር እንዳልተከሰተና ነዋሪውም ኢህአዴግ በአሸባሪዎች ስም ህዝቡን  እያሸበረው ነው በማለት ድርጊቱን መቃወሙን የተገኘው መረጃ አክሎ አስረድቷል።