Sunday, June 21, 2015

በባህርዳር ከተማ ትምህርታቸው ጨርሰው መንገድ ላይ ሲንቀሳቀሱ የተገኙት ወጣቶች ቦዞኔ እየተባሉ በጸጥታ አካላት ተገፈው ቤሻንጉል ወደሚገኘው የመንግስት እርሻ እንዲሰሩ መወሰዳቸው የተገኘው መረጃ አስታወቀ።



    ምንጮቻችን ከቦታው እንደገለፁት በባህርዳር ከተማ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎችና ኮሌጆች ተመርቀው ስራ ያላገኙት ወጣቶች እለታዊ ንሮአቸውን ለመምራት ሲንቀሳቀሱ ስለተገኙ ብቻ በስርዓቱ ካድሬዎችና የፀጥታ ሃይሎች ቦዞኔ ተብለው እንዲያዙ ከተደረገ በኋላ  ምንም ዓይነት የምግብና የህክምና አቅርቦት ወዳልተዘጋጀለትና ቤንሻንጉል ውስጥ ወደ ሚገኘው የመንግስት የጥጥ እርሻ ተወስደው በግድ እንዲሰሩ መደረጉን ተገለፀ።
    እነዚህ በግድ ተገፈው የተወሰዱት ወጣቶች መጀመርያውኑ ወደ ቦታው ሲሄዱ ስላልተቀበሉትና የሰሩትን ያህል በቂ ዋጋ ስለማይከፈላቸው ተማርረው ከካምብ እየሸሹ ወደ ጎረቤት አገሮች እየጠፉ ለመሄድ ሲሞክሩ በተለያየ መንገድ አደጋ እየደረሰባቸውና ህይወታቸው እያጡ መሆነቸውን ለማወቅ ተችሏል።
    መረጃው በማስከተል ከእርሻው ቦታ ጠፍተው ወደ ባህርዳር የተመለሱት አንዳንድ ግለሰዎች የመንግስት ንብረት ሰርቀው ነው የመጡት በሚል የሃሰት ውንጀላ ቢንያም ወርቁ፤ ፋንታሁን ይርሳው፤ ሙሉነህ ጥላሁን፤ ሙሉጌታ ታፈሰና ሌሎች ንፁሃን ወገኖች በፖሊሶች የታሰሩ መሆናቸው መረጃው አክሎ አስረድቷል።