Thursday, June 25, 2015

የሸራሮ ከተማ አስተዳዳሪዎች ወደ ከተማዋ የሚመደቡ የፋይናንስ ፅ/ቤት ሰራተኞች ምክንያቶች እየፈጠሩ እያሰርዋቸው እንደሚገኙ ተገለፀ።



   በሰሜናዊ ምእራብ ትግራይ ዞን ሸራሮ ከተማ በሚገኘው የፋይናንስ ፅ/ቤት ተሰማርቶ እየሰራ የቆየውን ጌታቸው የተባለ ግለ ሰብ በከተማ ውስጥ ከሚገኙ አስተዳዳሪዎች ስምምነት ስላልነበረው ብቻ ምክንያቶችን ደርድረው በተደጋጋሚ ሲያስሩትና ሲያንገላቱት ከቆዩ በኋላ መጨረሻ ላይ ያለአንዳች ወንጀል የሃሰት ክስ በመመስረት ራሳቸው መስካሪና ፍርድ ሰጪ በመሆን ለአምስት አመት እንዲታሰር ውሳኔ ስለወሰኑበት የከተማዋ ህዝቡ በመቃወም ላይ እንደሚገኝ መረጃው አስታወቀ።
    የህዝቡን ተቃውሞ መስማት የተሳናቸው የስርዓቱ ካድሬዎች ደስ ያላላቸውን ሰው አስረው ሌላ ሃደራ ተወልደ የተባለ አዲስ ሰራተኛ ወደ ፋይናንስ ፅ/ቤቱ እንዲገባ ቢወስኑም እሱም ራሱ የነሱን ተግባር አራማጅ ሆኖ ባለመገኘቱ ስራው ከጀመረ በኋላ ተንኮል ፈጥረው በመክሰስ ፍርድ ቤት እያመላለሱት እንደሚገኙ ምንጮቻችን ካደረሱን መረጃ  ለማወቅ ተችሏል።