Thursday, June 25, 2015

በባህር ዳር ከተማ የሚኖሩ በድግሪና በዲፕሎማ የተመርቁት ተማሪዎች የስርአቱን ባለስልጣናት ለከፍተኛ መኮንንነት እንድትማሩ ወደ ውትድርና ግቡ በማለት ሊያታልሏቸው በሞክሩበት ጊዜ ተቃውሞ እንዳጋጠማቸው ተገለፀ።


በደረሰን መረጃ መሰረት በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ የሚኖሩ ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች በዲግሪና በዲፕሎማ ተመርቀው ስራ ያጡት በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎች የገዢው ኢህአዴግ ባለስልጣናት ሰኔ 10 /2007ዓ/ም ለከፍተኛ መኮንነት እንድትሰለጥኑ መንግስት ሁኔታዎች አመቻችቶዋል በማለት። ወደ ውትድርና ሊቀጠሩ በዳረገው የማደናገሪያ ጥሪ በተማሪዎች ወላጆች ከፍተኛ ተቃውሞ እንዳጋጠማቸው ለማወቅ ተችሏል።
   መረጃው አክሎ የተማሪዎች ወላጆች ካቀረቡት ሃሳብ ልጆቻችን ያስተማርናቸው ህዝባቸው በትምህርት በማገልገል ሃገራቸው እንዲያለሙ፤ ድህነትና ድንቁርና ሊያጠፉ እንጂ ተምረው ወደ ውትድርና ገብተው ለጥቂት የገዢው ስርአት ባለ ስልጣናት እንዲያገለግሉ አንፈቅድም በማለት ነዋሪው ህዝብ በአንድ ድምፅ እንደተቃወመው መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።