Thursday, August 20, 2015

በርካታ ዲያስፖራዎች ወደ ነቀምቴ ከተማ ውስጥ ይገባሉ በማለት ለ400 ሰው ተብለው ሆቴሎች ቢዘጋጁም በወቅቱ የመጡት ግን አነስተኛ በመሆናቸው የሆቴሉ ባለቤቶች ለኪሳራ መጋለጣቸው ተገለጸ።




    የኢህአዴግ ካድሬዎች የነቀምቴን ህዝብ ነዋሪዎች ሰብስበው 400 የሚያህሉ የውጭ ዲያስፖራ ዜጎች ይመጣሉ በማለት በሆቴሎቹ ዝግጅት እንዲደረግ ቢገልፁም የተባሉትን ያህል መግባት ባለመቻላቸው የሆቴሎቹ ባለቤት ያዘጋጁትን ምግብና መጠጥ ተጠቃሚ በማጣቱ ምክንያት ለኪሳራ መጋለጣቸውን ከተገኘው መረጃ ለማወቅ ተችሏል። 
    የኢህአዴግ ባለስልጣናት በመገናኛ ብዙኃን ደጋግመው የዲያስፖራውን ቁጥር በማጋነን ለፖለቲካ ፍጆታ ይጠቀሙበት እንጂ መሬት ላይ ያለው እውነታ ግን እነሱ እንደሚሉት እንዳልሆነና በዲያስፖራው ስም ከህዝቡ ሀብት ለመንጠቅ የሚጠቀሙበት መላ መሆኑን ህዝቡ ስላወቀው በድርጊቱ ክፉኛ እያማራረ መሆኑንን የተገኘው መረጃ አስታውቋል።