Thursday, August 20, 2015

በአክሱም ከተማ ያለው መፍትሄ ያጣ የመሰረተ ልማት ችግር በህዝቡ ማህበራዊ ኑሮ ላይ ከፍተኛ ችግር መፍጠሩ ተገለፀ።



    በደረሰን መረጃ መሰረት በትግራይ ማእከላዊ ዞን፤ በአክሱም ከተማ ያለው ዓመታት ያስቆጠረ የመሰረተ ልማት እጥረት ስልጣን ላይ ያለው የኢህአዴግ ስርዓት መፍትሄ ማደረግ ባለመቻሉ ምክንያት ነዋሪዎቹ ለከፍተኛ የኑሮ ችግር መጋለጣቸው የገለጸው መረጃው በተለይም በከተማው ውስጥ ያለው የንፁህ ውሃ እጥረትና የመብራት መቆራረጥ የከተማው አስተዳዳሪዎች መፍትሄ ማድረግ ስለተሳናቸው ህዝቡ ወኪሎቹን እስከ ፌደራል መንግስት በመላክ ብሶቱን ባቀረበበት ግዜ መፍትሄ ያለው መልስ ማግኘት እንዳልቻሉ ለማወቅ ተችሏል።
    መረጃው በመቀጠል የአክሱም ከተማ ነዋሪ ለመጠጥና ምግብ ማብሰያ የሚሆን ውሃ አጥቶ ጥራቱን ካልጠበቀ የጉድጓድ ውሃና የተጠራቀመ ውሃ እየተጠቀመ በመሆኑ ለተለያዩ ውሃ ወለድ በሽታዎች መጋለጡን መረጃው አክሎ አስረድቷል።