Wednesday, September 23, 2015

ህ.ወሃት ኢህ.አ.ዴ.ግ ስለተዳከመ የቀደም አባሎቹን ለማስገባት እስካሁን ሙከራዎችን እያካሄደ መሆኑን ዶ/ር አረጋዊ በርኸ አስረድቷል፣



የህወሃት መስራችና በአሁኑ ጊዜ የኢትዮጵያ የጋራ ትግል የሸንጎ አባል የሆነው ዶ/ር አረጋዊ በርሄ ከኢሳት ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ በአሁኑ ጊዜ በከፍተኛ ሁኔታ ተዳክሞ የሚገኝ ሲሆን ከድርጂቱ ተሰናብተው የቆዩ አባሎቹን በማነጋገር ወደ ድርጂታቸው እንዲመለሱ ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ላይ መሆኑን አስታውቋል፣
ዶ/ር አረጋዊ በርኸ በቅርቡ የትህዴን ሊቀመንበር የነበረው ሞላ አስገዶም ወደ ህወሃት እጅ መስጠቱን ወይም ሌሎች የቀደም ነባር የህወሃት ታጋዮች መመለሳቸው ለህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የተወሰነ እስትንፋስ እንዲያገኝ ካልሆነ በስተቀር ችግሩን ሊፈታለት እንደማይችልና የጭቁኖች ትግል እንደሚያሸንፍ ገልጿል፣
ከትህዴን ጋር የቆየ ግንኑነት አለህ ወይ የሚል ጥያቄ ቀርቦለትም ፍስሃ ሃይለማሪያም የድርጂቱ ሊቀመንበር እያለ ግንኙነት የነበረው ሲሆን ሞላ አስገዶም ወደ ስልጣን ሲመጣ መቋረጡንና ሞላ በተደጋጋሚ ያቀርበው የነበረ ሲሆን ፈቃደኛ ሳይሆን መቅረቱን አስረድቷል፣
ዶ/ር አረጋዊ ጨምሮም ሞላ ይሁን ሌሎች የህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ አባላት ወደ ድርጂቱ ተመልሰው መግባታቸው የትግራይን ህዝብ እንደማያስወቅስና የትግራይ ህዝብና ህወሃትን አንድ አርጎ ማየት እንደ ህወሃት ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ዘረኛ መሆንና የትግራይን ህዝብ ችግር ላለማየት የሚደረግ በመሆኑ መታረም አለበት ብሏል፣
 ከህወሃት መስራቾች አንዱ የሆነው ዶ/ር አረጋዊ በርኸ ዲሞክራሲያዊ መሰረት ያለው ስርዓት ለመገንባት እንታገላለን  የሚሉ ሃይሎች ገዥው ስርዓት ኢ.ህ.አዴ.ግን ለማስወገድና የህዝብን ችግር ለመፍታት የሚደረገውን ትግል መፋጠንና መተባበር አለባቸው ሲል አሳስቧል፣