Wednesday, September 9, 2015

በኢ.ህ.አ.ዴ.ግ የመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ አዛዞች መካከል መነሳውን ስልጣን ያደረገ አለመግባባት ተፈጥሮ እንደሚገኝ ከመከላከያ ውስጥ የደረሰን መረጃ አመለከተ።



በመረጃው መሰረት በከፍተኛ የስርዓቱ የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች መካከል ሹመትንና ጥቅምን መነሻ ያደረገ ግጭት  ተነስቶ እንደሚገኝ የገለፀው መረጃው የአለመግባባቱ ጠንቅም የአማራ ብሄር ተወላጅ የሆኑ ጀኔራሎችና ኮሎኔሎች ለምን ማዕረግ አይሰጠንም? ሰላም አስከባሪ ለትግራይ ተወላጆች ብቻ ተከፋፍሎ እኛን ዙሮ የሚያየን አጣን? የማንታመን ስለሆንን ነወይ በወሳን ቦታ ላይ የማንቀመጥ? የሚሉና ሌሎችንም ጥያቄዎችና አቤቱታዎችን በማንሳታቸው መሆኑ ታወቋል።
በመጨረሻም አድሎውንና ልዩነቱን ኣየፈጠረ ያለው ሳሞራ የኑስ ሲሆን ግለሰቡ ለትግራይ ተወላጆች ብቻ ከፍተኛ ስልጣን በመስጠት በከፍተኛ ቦታ ላይ አስቀምጧቸዋል በማለት ቅሬታቸውን እንደገለፁ መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።