Wednesday, September 9, 2015

በመቐለ ከተማ ሲካሄድ የቆየው የህወሃት ጉባኤ ኢ-ዲሞክራሲያዊና የይስሙላ እንደነበረ ከስፍራው የሚገኙ ምንጮቻችን ከጉባኤው ተሳታፊዎች ካገኙት መረጃ ለማወቅ ተችሏል።



በጉባኤው ከተሳተፉ ሰዎች የተገኘው መረጃ እንዳመለከተው ከማዕከላዊ ኮሚቴነት በራሳቸው ፈቃድ ተሰናበቱ የተባሉት  ነባር ታጋዮች ለሚዲያ ሽፋን ሲባል ድርጅቱን ዲሞክራሲያዊ ለማስመሰል እንጂ ከሁለት አመት በፊት በማዕከላዊ ኮሚቴዎች መካከል የተፈጠረውን ልዩነትና አለመግባባት ምስጢሩን ለማጥፋትና ለመደበቅ የተጠቀሙበት የቡድኑ የይስሙላ አካሄድ መሆኑ ታውቋል።
     መረጃው ጨምሮም  ከነሃሴ 12 / 2007 ዓ/ም ጀምሮ የተካሄደ ጉባኤ ኢ-ዴሞክራሲያዊ አካሄድ ይከተል ስለነበር በጉባኤው የህወሃትን ድርጅት የሚመራው ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፅዮን ገብረ ሚካኤል መሆን አለበት የሚል በ20 የእጅ ብልጫ አሸንፎ እያለ መቀነስ አለባቸው ከተባሉት መካከል አቶ አባይ ወልዱ አንዱ መሆኑ እየታወቀ በኢ-ዲሞክራሲያዊ አካሄድ ህወሃት ማሌሊትን በሊቀመንበርነት እንዲመራ በይስሙላ ያሸነፈ አስመስለው እንዳቀረቡትና በጉባኤተኛው መካከልም የተፈጠረውን አለመግባባት ለማብረድ ጊዜ ተሰጥቶት ሊጠናቀቅ መቻሉን ለማወቅ ተችሏል።