Thursday, August 14, 2014

በአህፈሮም ወረዳ የሚኖሩ አርሶ አደሮች የሰብል ወቅት ካለፈ በኋላ ለአንድ ኩንታል ማዳበሪያ በ1340 ብር እንዲገዙ በአስተዳዳሪዎች እየተገደዱ መሆናቸውን ምንጮቻችን ከስፍራው አስረድተዋል።



በትግራይ ማዕከላዊ ዞን አህፈሮም ወረዳ የሚገኙ አስተዳዳሪዎች ከቀበሌ አስተዳዳሪዎችና ካድሬዎች ጋር በመሆን ለአንድ ኩንታል ማዳበሪያ በ1340 ብር ከፍለው ለሚገዙ አርሶ አደሮች የእርዳታ እህል እንደሚሰጡ ማዳበሪያ ያልገዙ ደግሞ በአስቸጋሪ የኑሮ ሁኔታ ላይ እየተሰቃዩ እያሉ ምንም አይነት እገዛና እርዳታ ከመንግስት እንደማይሰጣቸው ያካባቢውን ህዝብ በመሰብሰብ ቅስቀሳ እየሰጡ መሆናቸውን ምንጮቻችን አስረድተዋል።
   በተለይ  የዝባን ጒላ  ዋና አስተዳዳሪ  አለነ ተስፋማሪያም የህብረት ቀበሌ ሃላፊ ገብረዝጊሄር ክንፈ፤ የእንዳማሪያም ቀበሌ ሃላፊ ሽሻይ አዳነ ከጒላ-በሪሁ  ቀበሌ ሃላፊ  ገብረገርጊስ ፀጓሮ እንዲሁም ሽበሺ ገብረዝጊሄር ጋር በመሆን ህዝቡን በስራ ቀን ሰብስበው ማዳበሪያና ብድር ካልወሰዳችሁ እርዳታ የሚባል ነገር አታገኙም እያሉ በክረምት ወቅት ሰብሉ እንዳይታረምና አጥር እንዳይታጠር በማድረግ ወቅቱ ያለፈውን ማዳበሪያ እንዲገዙ እያስጨነቋቸው መሆኑን መረጃው አስታውቋል።