Tuesday, December 1, 2015

የአገራችን ወጣቶች የወያኔ ኢ-ዴሞክራስያዊ ስርኣት በመቃወም ወደ ትግራይ ህዝብ ዴሞክራስያዊ ንቅናቄ /ትህዴን/ ድርጅት ማሰልጠኛ ማእከል እየገቡ እንደሚገኙ ከማሰልጠኛው ስፍራ የደረሰን መረጃ አመለከተ።



    በዚህ በያዝነው ሳምንት ወደ ማሰልጠኛ ማእከል  ከገቡ ወጣቶች የተወሰኑ ስማቸውን ለመጥቀስ ያህል..
1.ተክላይ ገብረትንሳኤ ከትግራይ ክልል ማእከላዊ ዞን መረብ ለኸ ወረዳ አዲ ፍታው ቀበሌ
2. ፊልሞን ንጉሰ  ፀጋይ ኣረጋይ መለይ ማጀር ጠዓመ አረጋይ ከማእከላዊ ዞን  መረብ ለኸ ወረዳ በሪሃ ቀበሌ
3.ዕንበባ ሃይለ ከማእከላዊ ዞን አሕፈሮም ወረዳ ገርሁ ስርናይ ቀበሌ
4.ፍስሃየ ሓየሎም ከምስራቃዊ ዞን ኢሮብ ወረዳ ዓሊተና ቀበሌ
5.ቢንያም ተስፋይ ከምስራቃዊ ዞን ጉለመኸዳ ወረዳ ሸዊት ቀበሌ የሚባሉ የሚገኙባቸው ሲሆኑ፣
ወጣቶቹ በሰጡት ተመሳሳይ ሃሳብ። በለጋሽ አገሮች በእርዳታም ይሁን በስፍትኔት መልክ የመጣ ለድሃ ህዝብ  የተባለ  እርዳታ ገና በታለመበት ሳይደርስ በወርዳ እና ቀበሌ የሚገኙ የስርአቱ አስተዳዳሪዎች በመመሻጠር ወስድው በመሸጥ ለግል ጥቅማቸው እየተከፋፈሉት እንደሚገኙ በመግለፅ የቀረው የተውሰነ እህል ደግሞ ለቤተሰዎቻቸው እና ደጋፊዎቻቸው እያዋሉት እንደሚገኙ ጠቁመዋል።
በተለይ ወጣት መለይ ማጀር እና ፀጋይ አረጋይ  በሰጡት መረጃ። በአሁኑ ጊዜ  በአገራችን የሚገኙ አስተማሪዎች ደመወዛቸው ለመዉሰድ ቀን መቁጠር ካልሆነ በስተቀር በተነሳሽነት እንደማያስተምሩ የተመደበላቸው ክፍለ ጊዜ በሻሂ ቤትና  በሌላ ቦታዎች  እንደሚያሳልፉት ገልፀው በዚህ ተስፋ የቆረጠ ተማሪ ለይስሙላ ወደ ትምህርት ቤት ቢመላለስም እዚህ ግባ የሚባል  እዉቀት የሚጨብጥበት የትምህርት ስርኣት እንደሌለ ገልፀዋል።
በክፍተኛ ትምህርት ተቛማት የሚመረቁ ተማሪዎች ቢሆንም በመጨረሻ ስራ ኣጥቶው ሲንከራተቱ ስለሚታይ በአሁኑ ጊዜ ያለው ተማሪ የራሱ እጣ ፋንታ ከዚህ አያልፍም በማለት በትምህርት ላይ ያለው አተኩሮ እንዲዳከም እያደረገው እንደሚገኝ ጨምረው አስረድተዋል።