Monday, January 11, 2016

በመሰላ ከተማ ለኢህአዴግ ስረአት በሰላማዊ ሰልፍ ተቃውሞ ያደረጉ ተማሪዎች በፀጥታ ሃይሎች ሁለት ሲቆስሉ ከሃያ በላይ የሆኑ ደግሞ እንደታሰሩ ለማወቅ ተችሏል።



       የደረሰን መረጃ  እንደሚያመለክተው በምእራብ ሃረርጌ መሰላ ከተማ የሚገኙ ተማሪዎች ታህሳስ 26 2008 ዓ/ም ባካሂዱት  ሰላማዊ ሰልፋ ላይ እያሰሙት ከነበሩ መፈክሮች የታሰሩ ይፈቱ፤ የተገደሉ ወገኖች ለቤተሰቦቻቸው ካሳ ይሰጡ ፤ የሚልና ሌሎች መፈክሮች  እያሰሙ  በነበሩበት ጊዜ የአካባቢው አስተዳዳሪዎች በሉዋቸው የሚል ትእዛዝ ማወረዳቸውን ተከትሎ በከተማዋ የቀን ሰራ እየሰሩ ህይወታቸውን የሚመሩ ዜጎች ጨምሮ  የፀጥታ ሃይል ከፊታቸው ቆሞ ያገኙትን ሰው እየደበደቡበት በነበሩበት ጊዜ ይህንን በደል  ለመከላከል ሲሉ የቀን ሰራተኞቹም ሰላማዊ ሰልፍ እያካሂዱ ከነበሩት ተማሪዎች ጋር  በመቀላቀል ንደት በተሞላበት ሁኔታ ድንጋይ አንስተው  ግብረ መልስ ሊሰጡ እንደተገደዱ ለማወቅ ተችሏል።
      በዚህ በተፈጠረ ግጭት ምክንያት ደግሞ  ሁለት ተማሪዎች በፀጥታ ሃይሎች በመቁሰላቸው የተነሳ ወደ ጭሮ የሚባል ሆስፒታል  እንደተወሰዱና ከሃያ በላይ የሚሆኑ ተማሪዎች ደግሞ በዚያው ከተማ እንደታሰሩ ሰማቸው ለመጥቀስ ያልፈለጉ ተማሪዎች ለአሜሪካ ሬደዮ አማረኛ ቋንቋ  ሰርጭት በሰጡት ሃሳብ ለማወቅ ተችሏል።