Sunday, January 31, 2016

በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ የሚገኙ የኦሮሞ ተወላጆች የሆኑ ወታደራዊ መኮንኖች ከሚካሄደው ያለ ተቃውሞ ተያይዞ ለማስረና ለማባረር ሴራ በማሴር ላይ መሆናቸውን መረጃዎቹ ገለጹ።



 ገዥው የኢህአዲግ ስርአት በመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ለረጅም አመታት በማገልገል ላይ የነበሩት የኦሮሞ ተወላጆች የሆኑት ላይኞቹ ወታደራዊ  መኮንኖች በአዲስ ኣበባ ውስጥ በማስተር ፕላን ምክንያት በተለያዩ በክልል ኦሮምያ እየተካሄደ ያለው ከአንድ ወር በላይ የዘለቀውና  በገዥው ስርኣት ላይ ያነጣጠረው ሀይለኛ ህዝባዊ ተቃውሞ ውስጥ ትስስር ኣላቸው ተብለው በስርአቱ የተጠረጠሩት መኮንኖች ለማሰወገድ በሚል  የተለያዪ ሴራዎች በማሴር  ላይ መሆኑን ከመከላከያ ሰራዊት ውስጥ ሸልኮ የወጣውን መረጃ ኣስረድተዋል።

     መረጃው ጨምሮ በየአከባቢው በመካሄድ ላይ ያለው ትልቅ እንቅሳቃሴ ያለው ህዝባዊ ተቃውሞ ለማረጋጋት  በሚል ስርአቱ  በመወሰድ ላይ ያለው  የሃይል እርምጃ የማይመጣን ገደብ የሌለው ነው፣ “በማለት በሰራዊቱ የተነሳው ጥያቄ እንዲጎለብት በርከት ያሉ ወተደራዊ መኮንንኖች ኣስተዋጽኦና እጃቸው ኣለበት  የሚል ጥርጣረ በስርኣቱ እንዳለና፣  ከእነዚህ  የተጠረጠሩ መኮንነኖችም አንዳንዶቹ  በከፍተኛ የስራ ሃላፊነት ተቀምጠው በመስራት ላይ የቆዩና ያሉ  መሆናቸውን በመጥቀስ፣   በዚህ ሁኔታ ተያይዞም በእነዚህ  ላይ  የተላያዩ  ሴራዎች  በማሴር እንዲታሰሩና ከዚያም ጠቅልለወም ከስራቸው  እንዲባረሩ ተንኮል  በመሰራት  ላይ መሆኑን ለማወቅ ተችለዋል።
   






No comments:

Post a Comment