Sunday, January 31, 2016

የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች የግል ማረጋገጫ ይዞታ ካርታ ለመውሰድ ለካሬ ሜትር አራት ሺ ብር ያህል እንዲከፍሉ እቅድ እንደተዘጋጀ ከውስጥ አዋቂ ምንጮቻችን ያገኘነው መረጃ አስረድቷል።



      የነዋሪዎች የመሬት ይዞታ ማረጋገጫ  የሚባል ሰባ ሁለት ካሬ ሜትር ብቻ ሲሆን፣ በይዞታው ተከልሎ የአፈር ግብር ሲከፍሉ የቆዩትን ድርሻቸው እንደሆነ ለማረጋገጥና የግል ለማድረግ የተቀረ መሬት ተለክቶ ለእያንዳንዱ ካሬ ሜትር ሰዎስት ሺ ሰባት ሞቶ ስልሳ ብር እንዲከፍሉ በሊዝ እንዲዘዋወርላቸው የታቀደ መሆኑን መረጃው አስታወቀ።

      ከአሁን በፊት የመሬት ባለቤት የሆነው ሰው የይዞታ ማረጋገጫ ለማግኘት የሚከፈል የነበረውን ጠቅላላ 5 ሺ ብር ብቻ ሲሆን፣ አሰራሩን በመቀየር በካሬ ሜትር በሊዝ ደረጃ ተጨማሪ ገንዘብ ለመክፈል ገዢው የኢህአዴግ ስርአት ከዜጎች ከልክ በላይ ገንዘብ ለመቀማት ያለመ አዲስ የመላ አካሄድ መሆኑን ጉዳዩን የሚያውቁ የውስጥ አዋቂዎች ጨምረው ይገልፃሉ።



No comments:

Post a Comment