Wednesday, February 10, 2016

በሚቀጥለው 120 ቀናት ውስጥ አለም አቀፍ የእርዳታ ሰጪ ካልደረሱላቸው 10.2 ሚሊዮን ኢትዮጵያዊያን ዜጎዎች በራሃብ ለአደጋ እንደሚጋለጡ የተባበሩት ድርጅት አሳወቀ።



    የተባበሩት ድርጅት ጥር 22/5/2008 ዓ/ም ባቀረበው ሪፖርት በኢትዮጵያ አጋጥሞ ያለው ድርቅ ባለፈው አመት ጥቅምት ወር 2008 ዓ/ም 2.9 ሚሊዮን የነበረው የተረጅ ቁጥር፣ ባለፈው ጥር ወር 2008 ዓ/ም 8.2 ሚሊዮን ያለእርዳታ ሊውሉና ሊያድሩ የማይችሉ የተራቡ ህዝቦች እንደደረሱ የሚታውቅ ሆኖ፥  ጥር ወር  ደግሞ ከ10.2 ሚሊዮን ዜጎች አስቸኳይ እርዳታ ከላገኙ የሚበላ አጥተው አደጋ ላይ እንደሚውደቁ  አስታወቀ።
   በዚህ መሰረት በረሃብ የተገዱ የህፃናት ቁጥር 450 ሺ                       እንደደረሰ ከገለጹ በኋላ፥ የኢትዮጵያ መንግሰት ለእነዚህ ለተጎዱ ህብረተሰቦች የሚያቀርበው እገዛ እየተጓተተ በተፈጠረው ክፍተት አሳሳቢ በመሆኑ የተነሳ፣ በአሁን ወቅት አለም አቀፍ ህብረተሰብ በየቀኑ ከረዘመ ደግሞ በሳምንት ውስጥ ለእነዚህ በረሃብ ለተጎዱ ኢትዮጵያዊያን ዜጎች እርዳታ ማድረስ ካልቻለ፣ ከባድ የሰብአዊ ቀውስና አለመረጋጋት በኢትዮጵያዊያን ላይ ሊፈጠር እንደሚችል አስጠነቀቁ።


No comments:

Post a Comment