Thursday, March 3, 2016

የዓረና/መድረክ ተቃወሚ ድርጅት በትግራይ መቀለ ከተማ የጠራው ሰለማዊ ሰልፍ በህወሓት መሪዎች መታገዱ ተገለፀ።



     በመረጃው መሰረት የዓረና/መድረክ ተቃወሚ ድርጅት  በትግራይ መቀለ ከተማ  ህጋውነቱን ጠብቆ  እሁድ ለካቲት 20  /2008 ዓ/ም  የአገራችንን  ሁኔታ አስመልክቶ የጠራው ሰለማዊ የተቃውሞ ሰልፍ በህወሓት/ኢህአዴግ መሪዎች  መታገዱ ታወቀ።
  የዓረና/መድረክ ተቃውሚ ድርጅት ኣስቸኳይና መሰረታዊ መፍትሄ የሚያስፈልጋቸው  አገራዊና ክልላዊ ኣጀንዳዎች ብሎ ካሰቀመጣቸው   አራት ነጥቦችን፣  የአገር ሉኣላዊንት ይከበር፤  በረሃብ ለሚያልቁ ወገኖች መፍትሄ ይደረግላቸው፤ በኦሮም ክልል የተነሳው ህዝባዊ ቁጣ  ምክንያት መንግስት የሚወስደው የመግደል፤ የማሰር፤ የመደብደብና የሃይል እርምጃ ያቋርጥ፤ እና ሌሎችም ጥያቄዎች ሰለማዊ ሰልፍ ለማድረግ  ምላሽ እንዲያገኙ ፍቃድ ቢጠይቅም፣ የህወሃት/ኢህአዴግ መሪዎች ግን  ከመፍቀድ ይልቅ የማስፈራርትና የማስጠንቀቅያ በመስጠት ማገዳቸውን ታወቀ፣
   በመጨረሻ የትግራይ ህዝብ ከማንኛውም ህዝብ በላይ ለ17 አመታት ያካሄደው  መራር  የትጥቅ ትግል  ዴሞክራሲያዊ መብቶቹ እንዲከበሩለት ዋኞቹ ነጥቦች ሆነው፣  የስርኣቱ መሪዎች ግን የትግራይ ህዝብ አፍነው በመያዝ  ከማንኛውም በላይ ነፃነት አሳጥተው እንደሚገኙና በዚሁ ክልል ሰለማዊ ሰልፍ ማድረግ  እንደ ነውር መውሰዳቸው ለማወቅ ተችሏል።   

                            

No comments:

Post a Comment