Thursday, March 3, 2016

የገዢው ስርአት የፌደራል ፖሊስ አባላት የሚከዱ ቁጥር ከግዜ ወደ ግዜ እየጨመረ በመሄዱ ለተቀሩት ዝግ ስብሰባ ቢያደርጉላቸውም ሳይስማሙ መበተናቸው ታውቀዋል።



   በመረጃው መሰረት በአሁኑ ግዜ የገዢው ስርአት  የሚከዱ የፈደራል ፖሊስ   አባላት ቁጥር በመጨመሩ ምክንያት በዚህ የስጉ መሪዎች  ደግሞ ለተረፉት ዝግ ስብሰባ ቢያደርጉላቸውም  ሳይስማሙ  መቅረታቸውንና፣ ስብሰባውም  በአዲስ አበባ እንደተጀመረ  በተለይ ደግሞ የለመስማማት በላይኞቹ ሃላፊዎች ተባብሶ  በመቀጠሉ ሳይግባቡ እንዲበተኑ ምክንያት መሆኑን  ታውቋል።
  በባህርዳር ከተማም በድጋሜ  ስብሰባው ከየካቲት 13-16 / 2008 ዓ/ም የተከሄደው ሲሆን፣ በስብሰባው  ከተነሱት ነጥቦች  ደግሞ “ህዝቡ መንግስትን ለምን ጠላው?፤ መንግስት ህዝብን ለምን ያሰቃያል?፤ ለምን ህዝባችንን ግደሉ እንባላለን?፤ ወደ ህዝባችን እንድንተኩስ ለምን እንታዘዛለን?፤ ለእያንዳንዱ ህዝባዊ ቁጣን ለምን በጠመንጃ እናስታግሳለን?፤  ብለው በርካታ የፌዴራል ፖሊስ አባላት አስተያየታቸውን ሲያቀርቡ፣  አሁንም ስብሰባው  መቋጫ ሳይደረግለት መበተኑ መረጃው አስረድቷል።
    ከስብሰባው በኋላም አራት በከፍተኛ ስልጣን የነበሩ የፌዴራል ፖሊስ አባላት መክዳታቸው የታወቀ ሲሆን፣ እስካሁን የት እንደደረሱ መረጃ እንዳልተገኘ ለማወቅ ተችሏል።


No comments:

Post a Comment