የተገኘው
መረጃ እንዳመለከተው፣ የካቲት 21 /2008 ዓ/ም ከሰአት በኃላ
በአምቦ ወሊሶ ካምፓስ የተነሳው የእሳት ቃጠሎን ማን እንዳስነሳውና እንዴት እንዴት እንደተቃጠለ ለጊዜው ባይታወቅም፣ የስረአቱ
ደህንነት ኣባላት ሆን ብለው እንደለኮሱትና በዚህ ሳብያም
በህዝቡ ቁጣ ሊያነሳሱ ይችላሉ ብለው የጠረጠርዋቸው ተማሪዎችና መምህራን ወደ እስር ቤት ለማስገባት የተሴረ ተንኮል እንደሆነ
ምንጮች በመግለፅ ላይ መሆናቸወን ታውቀዋል።
በመጨረሻ መረጃው የስርኣቱ ባለስልጣኖች በህዝብ የተነሳው ቁጣ ሊያመልጡበት የሚችል እድል ስላጡ፣ ኣቅጣጫውን ለማስቀየስ
በተላላኪዎቻችው የተለያዩ ግምገማዎችና ችግሮችን በመፍጠር የጠረጠርዋቸውን ንፁሃን ወገኖች በማሰር ላይ መሰማራታቸው ለማወቅ ተችሏል።
No comments:
Post a Comment