Saturday, May 21, 2016

የፌደራል ዋና ኦዲተር መስራ ቤት ግንቦት 9 2008ዓ/ም ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባቀረበው ሪፖርት የፌደራል መንግስት ፅህፈት ቤቶች የ2007ዓ/ም የአመት ባጀት ሂሳብ አብዛኛዎችሁ የመንግስት ባጀት ተቀባዮች ድርጅቶች የሚያስደነግጥ የህግ ጥሰት እንደሚፈፅሙ ተገለፀ።



 የፌደራል ዋና አኦዲተር አቶ ገመቹ ዱቢሶ በምክር ቤቱ ተገኝተው ባቀረቡት ሪፖርት መሰረት ኣብዛኛዎችሁ የመንግስት ድርጅቶች በተደጋጋሚ በየ አመቱ የሚሰጣቸው አስተያየቶች ተግባራዊ ከማድረግ ይልቅ ወደ ከፋ የጥፋት መንገድ እየገቡ እንደሚገኙ የዚህ ምክንያት ደግሞ ተጠያቂነት የሚባል አሰራር ስለሌለ እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል።
 መጠየቅ አለባቸው ከሚባሉት የመንግስት ድርጅቶች ደግሞ በዝርዝሩ የተካተቱ ሲሆን። የገቢና ጉሙሩክ ባለ ስልጣን መስራ ቤት አስር የሚሆኑ ዩንቨርስቲዎች ተጠቃሾች ናቸው። በህግ በተደነገገ መሰረት የሂሳብ ሰነድ በወቅቱ እንደተወራረደ ለማጣራት በተደረገው የ አኦዲት ስራ በ94 መስራ ቤቶች በ11 ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤቶች 2.079 ቢልዮን ብር በደንቡ መሰረት በወቅቱ ሊወራረድ ኣንዳልቻለ ሪፖርቱ ያመለክታል።
በተሰበሰበው ሂሳቡ  የታዩት ዋና ዋና የአሰራር ግድፈቶች የሚባሉ በዝርዝር የቀረቡት ሲሆን በአራት መስራ ቤቶች የተሰበሰበው ሂሳብ ሌጀር ያልተዘጋጀላቸው 174 ሚሊዮን ብር እንደተገኘ ሲገልፅ በገቢና ጉሙሩክ መስራ ቤት ባሉት 3ት ቅርንጫፎችና ሌሎች 2ት መስራ ቤቶች ደግሞ ከ15.9 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ ተመዝግቦ ሪፖርት ሊደረግ የሚገባው ያለ አግባብ በተስብሳቢ ሂሳብ ተያይዞ እንደተገኘ አስረድቷል።
የመንግስት ገቢ በወጡት ህጎች መሰረት በአግባቡ ኣንደተሰበሰቡ ለማጣራት በተደረገው ኦዲት በ34 መስራ ቤቶች በገቢና ኩሙሩክ የሚገኙ 15 መስራ ቤትች በድምር 118.7 ሚሊዮን ብር ግዴታቸው ስላልተወጡ 211.930 ዶላር ግብር፤ ቀረፅና ታክስ እንዳልተሰበሰበ መረጃው ቸምሮ ገልፆዋል።


No comments:

Post a Comment