ባገኘነው መረጃ መሰረት በሃረማያ ዩንቨርስቲ የሚገኙ ተማሪዎች ገዢው የኢህአዴግ
ስርአት የፀጥታ ሃይሉን በማሰማራት እያፈናቸው እንዳለ ከገለፀ በሃላ። በዚህ ሳምንት ደግሞ በዩንቨርስቲው ቅጥር ግቢ የሚገኙ ተማሪዎች የምግብ ማቆም አድማ ያካሄዱ ሲሆኑ ይህንን ድርጊት ተከትሎ ደግሞ 5ት ያህል
ስማቸው ያልታወቁ ተማሪዎች በታጣቂዎች ከጊቢው አውጥተው በመውሰድ እስከ አሁን ድረስ የት እንዳሉ የታወቀ ነገር እንደሌለ ለማወቅ
ተችሏል።
የዩንቨርስቲው ተማሪዎች የታሰሩበት ምክንያት የተገለፀ እንኳ ባይኖርም። ፖለቲካዊ
ይዘት እንደሚኖረውና ከዚህ በፊት የሚደረግ የነበረው የተቃውሞ እንቅስቃሴ ግንኝነት ሊኖራቸው ይችላል ተበለው የተጠረጠሩት ታሰረው
ሊሆኑ እንደሚችሉ ቡዙ ወገኖች አስተያየታቸው በመግለፅ ላይ እንደሚገኙ
ታውቆዋል።
በሃረማያ ዩንቨርስቲ ከህዳር ወር ጀምሮ በመቀጠል ላይ ያለው ተቃውሞ ለጊዜው
የተዳከመ ቢመስልም በአሁኑ ጊዜ ደግሞ በዩንቨርስቲው ቅጥር ግቢ በረከት ያሉት የመከላከያ ሰራዊት ተሰማርተው እንደሚገኙና ግዜው
የሁለተኛ ሲሚስተር ፈተና እየተቃረበ ባለበት ጊዜ መከላከያ ሰራዊቱ አንድ ኣንድ ተማሪዎች እየታፈኑ በመሆናቸው የዩንቨርስቲው ተማሪዎች
በከባድ ስጋት ወድቀው እንዳሉ የተገኘው መረጃ አስረድቷል።
No comments:
Post a Comment