Saturday, May 21, 2016

በህገወጥ መንገድ ወደተባበሩት የአረብ ኤምሬቶች የሚጓዙት ኢትዮጵያውያን ቁጥር ከጊዜ ወደጊዜ እየጨመረ እንደመጣ ታወቀ።



መረጃው  እንዳስረዳው መንግስት ወደ ተባበሩት የአረብ ኤምሬቶች ይሁን ወደ ሌሎች አገሮች ለሚሄዱ አዲስ ህግ አውጥቻለሁ እያለ ቢሆንም እንኳ በየ እዕለቱ በመቶዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን ወደ ተለያዩ የአረብ አገሮች በህገወጥ መንገድ እየተሰደዱ የተለያዩ ችግሮች እየደረሱባቸው እንዳለ ተገልጿል።
   ይህ ያለህጋዊ የሚደረግ ስደት በአሁኑ ጊዜ አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል ያለው መረጃው ባለፈው አንድ አመት ብቻ በተመሳሳይ ሁኔታ የተጓዙና የተለያዩ ችግሮች የአጋጠሟቸው አምስት ሺህ የሚሆኑ ኢትዮጵያውያን መኖራቸውን በመግለፅ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር በበኩሉ በህጋዊ መንገድ በቪዛ እንዲወጡ ቢደረግም እንኳ ህገወጥ ስደቱ እንዳልቀነሰ አስታውቋል።
    የሰራተኞችና ማህበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴርና የህዝባዊ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት አቶ ግርማ ሸለመ ለጉብኝት ይሁን የቤት ሰራተኞችን በመቅጠር በቪዛ ብቻ ወደ ዱባይ የሚደረገውን ስደት ማገት አይቻልም ፣ህገወጥ ስደትን ባለመቆጣጠር የተነሳ ደግሞ በአሁኑ ጊዜ ብዙ ኢትዮጵያውያን ዜጎች በዱባይና በሌሎች አጎራባች አገራት በችግር ውስጥ ተቀርቅረው እንዳሉ አስታውቋል።
   በመጨረሻም የአረብ ኤምሬቶች የመገናኛ ብዙሃን በበኩላቸው በአሁኑ ጊዜ በእየእለቱ በትንሹ 500 ኢትዮጵያውያን በተለያዩ የአየር ጉዞ በመጠቀም ወደ አገሪቱ በመግባት ላይ እንደሚገኙ ገልፀዋል።

No comments:

Post a Comment