Monday, May 16, 2016

የዩናይትድ ስቴትስ የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሰቴት ዲፓርትመንት፤ በኢትዮጵያ የሚታየዉን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በተመለከተ አዲስ ዘገባ እንዳወጣ ታዉቀዋል።



የዲፓርትመንቱ ጸሐፊ ጆን ኤፍ ኬር የኢትዮጵያ መንግስት  በስቪል ማኅበረሰብ ላይ የሚያሳድረው ጫና እየጨመረ መምጣቱንና የመገናኛ ብዙኃን እና የኢንቴርኔት አገልግሎት የመጠቀም መብቶችም መጥበባቸዉን እንዲሁም የተቃዋሚ ድምፆች መጨፍለቅ ሠዎችን መግደል እና ከአገር እንዲወጡ ማዋከብ ዋነኛዉ መሆኑን መናገራቸዉ ዘገባዉ ያመለክታል።
  ዘገባው ጨምሮ እንዳስረዳው በኢትዮጵያ የተቃዉም ፖለቲካ ፓርቲ አባል የሆኑትን እና ጋዜጠኞችን ማስፈራራት ማሰር መግረፍ እና ማሰቃየት፣ ከዛም አልፎ ያለምክንያት መግደልን ጨምሮ ሌሎች የሰባዊ መብት ጥሰቶች ሁሉ በመንግስት የፀጥታ ሃይሎች በንፁህ ህዝብ ላይ እየተፈፀመ እንደሚገኝ ዘገባው ጨምሮ ገልፀዋል።







No comments:

Post a Comment