Monday, May 16, 2016

በዚህ ሳምንት በርከት ያሉ የኢህአዴግ ወታደሮች ስርአቱን በመቃወም ወደ ትህዴን ማሰልጠኛ ማእከል ተቀላቀሉ።



ከተቀላቀሉት ወታደሮች ውስጥ የተወሰኑትን ለመጥቀስ ያህል፣ 1ኛ ወታደር ጥጋቡ ሞላ የደቡብ ህዝቦች ብሔር የሆነ አሁን በመከላከያ በማእከላዊ እዝ ከ22ተኛ ክፍለ ጦር ከአንደኛ ሬጅመንት ከአንደኛ ሻንበል ከጋንታ ሁለት ቲም አራት የነበረ።

2ኛ ወታደር ሙሉጌታ ሰዩም የአማራ ብሔር የሆነ   ከ22ኛ ክፍለ ጦር አራተኛ ሬጅመንት ሻንበል አራት ጋንታ ሶሰት ቲም አራት የነበረ፣
                                         
3ኛ  ወታደር መለስ ባንቲ የአማራ ብሔር የሆነ ከሰሜን እዝ 20ኛ ክፈለ ጦር ሶሰተኛ ሬጅመንት ሻምበል አንድ የነበረ፣

4ኛ  ወታደር ወልደገብርኤል ገብረሚካኤል የትግራይ ብሔር  ከሰሜን እዝ 11ኛ ክፍለ ጦር ሶስተኛ ሬጅመንት የነበረ፣

5ኛ ሃምሳ አለቃ አደም ሙሃመድ የአማራ ብሔር የሆነ ከሰሜን እዝ 13ኛ ክፍለ ጦር የነበረ፣

6ኛ ወታደር ኤቢሳ አብደሰላም የአፋር ብሔር ከ25ኛ ክፍለ ጦር ሶሰተኛ ሬጅመንት አንድኛ ሻምበል  የነበረ፣
  
7ኛ ወታደር አስማማው አፃሴ ከደቡብ ብሔረሰቦች ኦሞ ዞን ሚሊ ወረዳ ከንቲባ ቀበሌ የነበረ፣

8ኛ ወታደር አወል ሙሁዲን የአማራ ብሔር ከ25ኛ ከፈለጦር ሰድሰተኛ ሬጅመንት አንደኛ ሻምበል የነበረ፣ 
9ኛ ወታደር ተመስገን አግደው ከበንሻጉል ጉሙዝ ብሔር ከሰሜን እዝ ከ11ኛ ክፍለ ጦር አራተኛ ሬጅመንት ሶሰኛ ሻምበል አንደኛ ጋንታ አራተኛ ቲም የነበረ፣
10ኛ  ወታደር ኢሳያስ አለሊ የአማራ ብሔር ከማዕከላዊ  እዝ ከ22ተኛ ክፍለ ጦር አራተኛ ሬጅመንት የመካናይዝድ  ምድብተኛ የነበረ፣

11ኛ  ወታደር ክፋሎም ገብረመሰቀል የትግራይ ብሔር ከ11ኛ ክፍለ ጦር አራተኛ ሬጅመንት ሶሰኛ ሻምበል አንደኛ ጋንታ ሶሰተኛ ቲም የነበረ፣

12ኛ ወታደር አበበ አሸብር የአማራ ብሔር ከማእከላዊ እዝ 31ኛ ክፍለጦር አራተኛ ሬጅመንት ሰለያ የነበረ፣
13ኛ ወታደር ግርማይ ገብረሰላሴ ከትግራይ ብሔር ከማእከላዊ እዝ ከ31ኛ ክፍለጦር አራተኛ ሬጅመንት ከሁለተኛ ሻምበል  አንደኛ ጋንታ አራተኛ ቲም።
 
14ኛ  ወታደር በሽር የሴፍ የሱማሌ ብሔር የሆነ ከማእከላዊ እዝ ከ22ኛ ክፍለጦር ሰምንተኛ ሬጅመንት ሁለተኛ ሻምበል  ሁለተኛ ጋንታ የሚገኝ ሆኖ ።እሱም ወደ ትጥቅ ትግል ለመሰለፍ ምክንያት ከሆኑት በጋራ ከሰጡት ሃሳብ። እኛ ወታደሮች የገዢው ሰርአት እድሜ ማራዘሚያ  ከምንሆን በዚህ ወቅት አጋጥሞት ያለው የእርስ በርስ ግጭትና ቀወሰ  ወደ ከፋ አደጋ ሳይወጣ ጠመንጃ  ታጥቀን አገርንና ህዝብን ለማዳን የድርሻችንን ለመወጣት ተሰልፈናል ብለዋል።

 አደም ሙሃመድና በሸር የሴፍ በጋራ በሰጡት ሃሳብ ደግሞ በአሁን ወቅት የአገሪቱ ወታደር ሆነህ ልትኖር አሰቸጋሪ ነው በማለትና  ቀጥለውም ሰራዊቱ ለሰላም ማሰከበር የሚላከውና የሚሰጠው ማእርግና ሌሎች ግልፅ የሆነ ልዩነቶች ሰለሚያደርጉ አንድነቱ የተበታተነ በአጠቃላይ እምነት ወኔ አድሮበት በሰራዊቱ ሊቆይ የሚፈልግ የለም፣ በተለይ በአሁን ጊዚ በመላ የአገሪቱ አካባቢዎች  ባሉት  ግጭቶች የተነሳ በመከላከያ ሰራዊት ከፍተኛ  ጥያቄና እርሰበራሳቸው ባልተማመኑበት  ሁኔታ በመድርሱ በየጊዜው ምርጫቸው  ከመከላከያ ትተው ይወጡ እንዳሉ አሰታወቀ።

No comments:

Post a Comment