Monday, May 16, 2016

በአገራችን ኢትዮጵያ በተለያዩ አካባቢዎች የጎርፍ አደጋው በሂወትና በንብረት ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑንና 400 ሺሕ ሰዎች ለጉዳት እንደሚጋለጡ ተገለፀ።



በተለያዩ የአገሪቱ አካባቢዎች በመጣል ላይ በሚገኘው ከባድ ዝናብ ምክንያት የተፈጠረው ጎርፍ የሰው ሕይወት ከመቅጠፍ ተጨማሪ በማሳ ላይ የሚገኙ ሰብሎችና የመንገድ አውታሮች ላይ ጉዳት እያደረሰ እንደሚገኝ የሚታወቅ ሲሆን ሰሞኑን በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ሳያቋርጥ የጣለው ዝናብ ባስከተለው ጎርፍ ምክንያት የዘጠኝ ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በርካታ የቤት እንስሳትና ከ560 ሔክታር በላይ በሆነ ማሳ ላይ የሚገኝ ሰብል መውደሙንና  ከሮቤ ወደ ጎሮ የሚወስደውን መንገድ በመስበሩ የትራንስፖርት እንቅስቃሴም መቛረጡን መረጃው ጨምሮ ገልፀዋል።
  በተመሳሳይ በምሥራቅ ሐረርጌ የጣለው ዝናብ ደግሞ የሁለት ሕፃናትን ሕይወት ሲቀጥፍ። ከድሬዳዋ ወደ ሐረር የሚወስደውን መንገድ መስበሩን ገልፆ ከሞጆ ወደ ሐዋሳ በሚወስደው መንገድ መቂ አካባቢ የጣለው ከፍተኛ ዝናብም መንገዱን ከባድ ደለል በማልበሱ የትራንስፖርት ፍሰቱ ላይ እንከን መፈጠሩ ተመልክቷል፡፡
  ከዚህ ባሻገርም አሰላ ከተማን የመታው ጎርፍ የከተማውን መንገዶች መሰባበሩ ተገልጿል ዝናቡ በአፋር በሰሜን ሸዋ (ሸዋ ሮቢት) ስልጤ ዞን ጂግጂጋ ድሬዳዋ አርባ ምንጭ ደቡብ ወሎና በሌሎችም የአገሪቱ ክፍሎች ከፍተኛ ጉዳት በማድረስ ላይ የሚገኝ ሆኖ በአገሪቱ 400 ሺሕ ዜጎች ጉዳት እንደሚደርስባቸውና 180 ሺሕ የሚሆኑት ደግሞ ከመኖሪያቸው እንደሚፈናቀሉ መረጃው የጠቆመ ሲሆን በመንግስት በኩል ግን ለዚህ ሰለባ የሆኑ ዜጎች በቂ እርዳታ እያደረገላችው አለመሆኑን የደረሰን መረጃ ያመለክታል።

No comments:

Post a Comment