Monday, May 16, 2016

በትግራይ ማዕከላዊ ዞን የሚገኙ የፍትህ አካላት ነፃ ሆነው በቀናነት እንዳይሰሩ በወያኔ ኢህአዴግ ባለስልጣናት ጫና እየደረሰባቸው እንደሆነ ታወቀ።



በትህዴን የስልጠና ክፍል መረጃ መሰረት በአሁኑ ጊዜ ከተለያዩ የአገራችን አቅጣጫዎች የመጡ ወታደሮችና የከፍተኛና የመለስተኛ ደረጃ ተማሪዎችና ሌሎችም በየቀኑ ወደ ትህዴን የስልጠና ማዕከል እየጎረፉ መሆናቸውን የገለፀው መረጃው ነዋሪነቱ በትግራይ መካከለኛ ዞን አሕፈሮም ወረዳ ላዕላይ መጋርያ  ፀብሪ ቀበሌ የሆነ ገብረዋህድ ሃይሉ የተባለ አንዱ ሲሆን ዳኛ ሆኖ እየሰራ በነበረበት ጊዜ በቀናነት የሚሰራበት ቦታ በመጥበቡና በላዩ ላይ የተለያዩ ተፅዕኖዎች ይደርስበት እንደነበር በመግለፅ ይህንን ፍትሐዊ ያልሆነ አካሄድ ይቃወም በነበረበት ወቅት ደግሞ ብዙ ማስፈራራትና በገዛ አገሩ በነፃነት ሊንቀሳቀስ ባለመቻሉ ጠበጃ ታጥቆ ጭቁንነቱንና የህዝቡን ተጨቋኝነት ለመፍታት ወደ ትህዴን እንደተቀላቀለ ከደረሰን መረጃ ለማወቅ ተችሏል።
    በመጨረሻም ህዝቡ በአሁኑ ወቅት በፀጥታ ኃይሎች እየተጠበቀና እየተገረፈ በከባድ ስጋት ውስጥ እንደሚገኝ የደረሰን መረጃ ገልጿል።

No comments:

Post a Comment