Saturday, May 21, 2016

ከአዲስ ኣበባ የተፈናቃሉ አርሶ ኣደሮች በዚህ በቅርብ ግዜ የፀደቀውን መምርያ በመቃወም አቤቱታቸውን እንዳስሙ ታወቀ።



   የአዲስ ኣበባ ከተማ የካቤኔ  አስተዳደር የካቲት 16  2008ዓ.ም ተሰብስቦ በነበረበት ጊዜ  የመሬት ጥያቄ ኣቤቱታ ሲቀርብለት  የተወሰደውን መሬት መተኪያ የሚሆን መሻሻያ ኣድርጌያሎህ  ቢልም  እንኳ ካቢኔው ከዚህ መምርያ  በተጨማሪ የካሳ ክፍሊት ኣስጣጥ ማሻሻያ ሊያደረግ የልማትና የመሬት የማኔጅመንት ፍትህ ፅህፈት ቤት ውሳኔ ለማቅረብ በእርሻ የሚገኙ ዘሮችና  ተክሎች ካሳ የሚሰጥ    የከተማ መሬትና የአከባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የውሳኔ ሃሳብ ለማቅረብና መተኪያ ህንፃዎች በሚመለከት ደግሞ የኮንስታራክሽን  ህንፃ ጽህፈት ቤት እንዲሁም የንግድ ጽህፈት ቤት የውሳነ ሃሳብ እንዲያቀርብ በእለቱ ትእዛዛ እንዳስተላልፈ ታወቀ።
  ይህ ተግባራዊ ባለመሆኑ ደግሞ  በእርሻ የሚተዳደሩ ነዋሪዎች  በአዲስ ኣበባ  ውስጥ ኮሚቴ በማቋቋም  በዚህ ቅርብ ግዜ ለአዲስ ኣበባ ከንቲባ ባቀረበው ደብዳቤ የአዲስ ኣበባ አስተዳደር ባወጣው የመሻሻያ ነጥብ ተደርጎላቸው የተባሉ ነጥቦች ግን ትኩረት ኣልተደረገለትም በማለት አዲሱ የወጣው መምርያ ይሁን በ2004ና በ2006 ዓ/ም የወጡ መምርያዎች እንዳሉና ለአንድ ገበሬ 250 ካሬ ሜትር ሊሰጥ የተሰጠ መመርያ ቢሆንም  እስካእሁን ድረስ ተግባራዊ እንዳልሆነ ለማወቅ ተችለዋል።
     በአዲስ ከተማ በእርሻ ላይ የተሰማሩ  ወገኖች ልማት ምክንያት  በማድረግ በመፈናቀል ላይ የሚገኙ አርሶ አደሮች  ግንቦት 10 ቀን 2008 ዓ/ም ያቋቋሙት ኮሚቴ በፀደቀው መምርያ ተቃውሞ  ያቀረበ ቢሆንም   ኮሚቴው ለአንድ አርሶኣደር  የሚከፈለው ካሳ ከሁለት ሚልዮን ብር ማነስ የለበትም በማለት በአርሶ ኣደሮች አስተባባሪ በሆኑት በአቶ ተስፉ በኩል ኣቤቱታ ቢያቀርቡም ለተፈናቃያቹ የሚከፈለው ካሳና መተኪያ ቦታ ጥቂት በመሆኑ  ለሽግር እየተጋለጡ መሆናቸው በማስታወስ ችግሩ ደግሞ እስካአሁን ድረስ እንዳልተፈታ ታወቀ።

  

No comments:

Post a Comment