Saturday, May 21, 2016

በሰሜን ሸዋ ዞን ማጀቴ ከተማ የተነሳው የተቃውሞ ሰልፍ ተጠናክሮ እየቀጠለ መሆኑ ተገለፀ።



   በሰሜን ሸዋ ዞን ገምዛ ወረዳ የሚኖሩ የማጀቴ ንዑስ ወረዳ ነዋሪዎች የገምዛ ወረዳ ይመለስልን በሚል የተነሳ ተቃውሞ እየሰፋ መሄዱን ተከትሎ የመንግስት ሰራተኞች አካባቢውን ትተው ወደዋና ከተማዋ እንደሄዱ ታውቋል።
    የክልሉ የፍትህ ኃላፊና የህዝብ ግንኙነት ተጠሪ ወደ አካባቢው ተንቀሳቅሰው ለህዝቡ ባነጋገሩበት ወቅት የነዋሪው ህዝብ ጥያቄ ተቀባይነት እንደሌለው በመግለፃቸው በእለቱ ኃይለኛ ህዝባዊ ተቃውሞ እንደተነሳ የገለፀው መረጃው በዚያን ጊዜ አካባቢው የጦርነት ቦታ መስሎ እንደዋለ ተገልጿል፣የቀበሌው ሊቀመንበር የሆኑት አቶ አባቡ እንዲሁም የፖለሲ አዛዥ ኢንስፔክተር ሸዋቀናው ከአካባቢው መልቀቃቸውን ህዝቡ ደግሞ ወደሊቀመንበሩ ቤት በማምራት ንብረታቸውን ሙሉ በሙሉ እንዳወደመው መረጃው አስረድቷል።
    በሌላ በኩል የአካባቢው ወጣቶችና ተማሪዎች ተደራጅተው የመንግስት ሰራተኞች ከአካባቢው ለቀው እንዲሄዱ ተፅዕኖ እንደፈጠሩና በንዑስ ወረዳዋ የሚገኙ የስድስት ቀበሌዎች ወጣቶች የመንግስት ሰራተኞች ከአካባቢው ከመልቀቃቸው በኋላ እራስ በራሳቸው እየተዳደሩ እንደሚገኙ የአካባቢው ነዋሪዎች ሲናገሩ መሰንበታቸውን ተገልጿል።


                    


No comments:

Post a Comment