Thursday, June 16, 2016

በትግራይ ደቡብ ዞን እንዳምኾኒ ወረዳ የሚገኙ ከ200 በላይ ወጣቶች በስራ አጥነትና በመልካም ኣስተዳደር እጦት ለከፋ ችግር ወድቀናል በማለት በስርአቱ ላይ ያላቸውን ጥላቻ በመግለፅ ላይ መሆናቸውን መረጃዎቻችን ከአከባቢዉ ገለፁ።



በመረጃው መሰረት በትግራይ ክልል  ደቡባዊ ዞን እንዳምኾኒ  ወረዳ ጣብያ ሽምጣ የሚገኙ  ከ200 በላይ  ወጣቶች  በስራ እጥነትና በመልካም አስተዳደር እጦት   ለከፋ ችግር   መጋለጣቸው  በመጥቀስ  የስርአቱ ካድሬዎችና አስተዳዶሮች ደግሞ ጉቦ ለሰጥዋቸው ለመንግስት ሰራተኞችና   በቀበሌው ለማይኖሩ   ዜጎች   እርሻ መሬት በማደል ላይ መሆናቸውን  ታወቀ።
    መረጃው ጨምሮ  የወረዳው  ኣመራር የሆነችው አስካል ገብረመሰቀል  እርሻ መሬት  በመከፋፈል ላይና በመልካም ኣስተዳደር ከፍተኛ  ችግር እንዳለና  አስተዳዳሪዎቹም በአድልዎ እንደሚሰሩ  በሚድያ  መግለፅዋን ምንም,   ፋይዳ የለውም ።  በውቅቱ   የስርአቱ ወንጀለኞችና ካድሬዎች  ወደ ህግ ቀርበው   ህጋዊ እርምጃ ይወሰድባቸው በማለት    ወጣቶቹ   በስርአቱ ላይ ያላቸውን  ተቃውሞ  መግለፃቸ ታወቀ።


No comments:

Post a Comment